April 23, 2024 – Konjit Sitotaw 

ኢሠማኮ፣ ዘንድሮ ሚያዝያ 23 ቀን በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም ሠራተኞች ቀን በአዳራሽ ውስጥ ብቻ እንዲከበር መወሰኑን አስታውቋል።

ኢሠማኮ፣ በበዓሉ የአከባበር ሁኔታ ላይ እዚህ ውሳኔ ላይ የትደረሰው፣ “የአገሪቱን አጠቃላይ ኹኔታ” እና “በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” ሥር የሚገኙ አከባቢዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደኾነ ገልጧል።

ኾኖም ይህ የበዓሉ አከባበር፣ ባሕርዳር፣ ኮምቦልቻና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ከተሞችን እንደማይጨምር ኢሠመኮ አመልክቷል።

የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት፣ እስከ በዓሉ ድረስ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሠራተኞችን ተወካዮች በሠራተኛው ጥያቄዎች ዙሪያ እንዲያነጋግሩ መወሰኑንና ጥያቄው ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት መቅረቡን ኢሠማኮ ጨምሮ ገልጧል።