
ከ 4 ሰአት በፊት
የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በአገሪቱ ቲክቶክን ሊያግድ የሚችል አወዛጋቢ አዋጅን አጽደቀ።
አዋጁ የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ የማህበራዊ ትስስር ገጹን ድርሻ በ9 ወር ውስጥ የማይሸጥ ከሆነ ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ ያግዳል።
አዋጁ ወደ ፕሬዝዳንት ባይደን የተመራ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አዋጁ ኋይት ሃውስ እንደደረሰ ፊርማቸውን አኑረውበት ሕግ እንደሚያደርጉት ተናግረው ነበር።
ባይትዳንስ ለዚህ ውሳኔ ፈጣን መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ለቢቢሲ ተናግሯል።
ቀደም ብሎ ግን ቲክቶክ በጫና ለማሸጥ የሚደረግ ሙከራን አጥብቆ እንደሚቃወም ተቋሙ ገልጿል።
አሜሪካ ቲክቶክን እንዲሸጥ ባይትዳንሳ ላይ ጫና አድረጋ ቢሳከላት እንኳን ለሽያጩ ሂደት የቤጂንግ ባለስልጣናት ይሁንታ ያስፈልጋል። ሆኖም ቻይና ይህንን አይነቱን ውሳኔ እንደምትቃወም ገልጻለች።
ተንታኞች ይህ ሂደት ዓመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ይገልጻሉ።
ይህን አዋጅ ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት አብለጫዎቹ ደግፈውታል። 79 የምክር ቤት አባላት ሲደግፉት 18 የሚሆኑት ደግሞ ተቃውመውታል።
የምክር ቤት እውቅ የሪፐብሊካን እና የደህንነት ኮሚቴ አባል የሆኑት ማርኮ ሩቢዮ “ለአመታት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በአሜሪካ ዝነኛ የሆነውን መተግበሪያ እንዲቆጣጠረው ፈቅደናል። ይህ ሁኔታ በአደገኛ ሁኔታ የቅርቡን ብቻ የተመለከተ ነው” ብለዋል።
ጨምረውም አዲሱ አዋጅ ቻይናውያን ባለቤቶቹ መተግበሪያውን እንዲሸጡ የሚጠይቅ እንደሆነ ጠቅሰው ለአሜሪካ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ተናረዋል።
- አቶ ጌታቸው ረዳ ከብልፅግና ጋር ስለመዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ምን አሉ?ከ 5 ሰአት በፊት
- ዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የምትልክበት ሕግ ምንድን ነው? ተፈጻሚነቱስ በማን ላይ ነው?ከ 5 ሰአት በፊት
- በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በደረሰ የጀልባ አደጋ 16 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ሞቱ23 ሚያዚያ 2024
ይህ አዋጅ ከመጽደቁ በፊት ቢቢሲ ስለ አዋጁ ቲክቶክን ጠይቋል። ኩባንያው ባለፈው ሳምንት በሰጠው አስተያየት አዋጁ የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያን የመናግር መብትን የሚነጥቅ ነው ብሏል። ጨምሮም በየዓመቱ 24 ቢሊዮን ዶላር አስተዋጾ የሚያደርጉ 7 ሚሊዮን የንግድ ስራዎችን እንደሚጎዳ ጠቅሷል።
የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሺ ዙ ቼው ይህንን ማህብራዊ ትስስር ገጽ ለመታደግ ሕጋዊ መብቱን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት መንገድ እንደሚጠቀም ገልጿል።
በአሜሪካ በሚገኘው ሪችሞንድ ዩኒቨርሲቲ የህግ ፕሮፌሰር የሆኑት ካርል ቶቢያስ ለቢቢሲ ሲናገሩ ይህ ፈጥጫ ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል ብለዋል። “ወደ ሁለት ዓመታት አከባቢ ይወስዳል” ሲሉ ተናግረዋል።፥
ጨምሮም የባይትዳንስ ድርሻ የሚገዛ የአሜሪካ ኩባንያ በ9 ወር ውስጥ ማግኘት አዳጋች እንደሆነ አንስተው ይህም ሂደቱን ሊያጓትተው እንደሚችል ገልጸዋል።
በአሜሪካ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መረጃ በቻይና እጅ ላይ ወድቋል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። በዚህም ምክንያት አሜሪካ በአሜሪካ የሚገኘው የቲክቶክ ቅርንጫፍ ቤጂንግ ከሚገኘው ኩባንያ እንዲነጠል ትፈልጋለች።
ሆኖም ባይትዳንስ ቲክቶክ የቻይና ወይም የሌላ ሀገር ወኪል አይደለም ሲል ይከራከራል።