April 24, 2024 

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ ያስቀመጣቸው መፍትሔዎች “በሙሉ” በገዢው ፓርቲ የተያዙ ናቸው አለ

በኢትዮጵያ ውስጥ የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው እና በአገሪቱ ፓርላማ “አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሠ) ዛሬ ረፋድ የብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት ለአገሪቱ ስብራት ያስቀመጣቸው መፍትሔዎች በሙሉ በገዢው ፓርቲ አለ።

አዲስ ማለዳ ከድርጅቱ ይፋዊ የኤክስ ገጽ እንደተመለከተችው “የብልጽግና ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት” የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ እና ለትውልድ የተሸጋገሩ ቀውሶች ለመፍታት ፍኖተ ካርታውን “አሳትሟል” በማለት ገልጿል።

የብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ በመግለጫው “የታሪክ ስብራቶቹን” ለመጠገን ፖለቲካዊ ችግሮችን በአገራዊ ምክክር፤ እንዲሁም በሽግግር ፍትሕ እና በተሐድሶ ለመጠገን መስራት እንደሚገባ መግለጹን አዲስ ማለዳ ዘግባ ነበር።

ታጣቂ ቡድኑ “ሦስቱም ሂደቶች ሙሉ በሙሉ በገዢው አካል ባለቤትነት የተያዙ እና በጥቃቅን የሚተዳደሩ ናቸው” ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልታለች። “እንደ የሽግግር ፍትህ እና ብሔራዊ ውይይት ያሉ የቃላት ቃላቶችም ሕዝቡን ለማደናገር እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እጅ መንሻ ነው” ሲል የኦርሞ ነጻነት ግንባር አስታውቋል።

ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት “ሕግ የማስከበር ሥራ” ያለውን አስከፊ ውጤት “ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባል”- ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት 
ተጨማሪ ያንብቡ https://addismaleda.com/archives/36504

By  አዲስ ማለዳ

 –

24/04/2024

በትግራይ ክልል ያለው የልማት ስራ “መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት” አይደለም ተብሏል

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከተመካከረ በኋላ ባወጣው መግለጫ “በስምምነቱ መሠረት የህሐት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው” ብሎ “የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት” ሲል አስታውቋል።

ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ በረጅም የፖለቲካ ዕድሜዋ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ባለመቻሏ በርካታ “የታሪክ ስብራቶች” ተከስተዋል ብሏል። “የታሪክ ስብራቶቹን” ለመጠገን “ነባሩን ፖለቲካዊ ችግር በሀገራዊ ምክክር መፍታት፤ የቅርብ ዘመናችንን የፖለቲካ ችግር ደግሞ በሽግግር ፍትሕ እና በተሐድሶ ማረም” በሚል አገራዊ ምክክሩን፣ የሽግግር ፍትህ ሂደቱን እና የተሃድሶ ስራዎች ላይ መንግስት የሰራቸውን ስራዎች ገልጿል።

ግጭቶችን በስምምነት የመፍታት ልማድ “አለመኖርን ቀይሯል” የተባለው የፕሪቶሪያ ስምምነት ደም አፋሳሽ ጦርነትን በማስቆም የመልሶ ግንባታ ስራዎች እንዲሰሩ ማድረጉን አዲስ ማለዳ ከብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ መግለጫ ተመልክታለች። 

የደህንነት ምክር ቤቱ “ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉ” ያላቸውን እና በስም ያልጠቀሳቸው አካላት “ሁላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይኖርብናል” በማለት አሳስቧል። በተጨማሪም “ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባልና” ሲል አጽንዖት ሰጥቷል። 

በትግራይ ክልል፤ የሰላም ድርሻው ታላቅ በመሆኑ “መንግሥት ከሚጠበቅበትም አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው” የተባለ ሲሆን “ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም” ሲል የደህንነት ምክር ቤቱ አስጠንቅቋል


“ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍተው በጽንፈኞች እና በግጭት ጠማቂዎች ወደ ጦር ዐውድማ የሚማገዱበት አጋጣሚ አለ” ያለው ምክር ቤቱ፤ መንግስት “እንቅስቃሴያቸው ሕገ ወጥ ስለሆነ ብቻ ጉዳዩን በጉልበት ብቻ ይፈታ ማለት እንደሌለበት ይገነዘባል” ብሏል። ለዚህም ማኅበረሰቡን ተቀላቅለው ሰላማዊ ሕይወት ለመኖር ፍላጎት ያላቸውን ታጣቂዎች ሁሉ ለመቀበል መንግሥት ፈቃደኛ መሆኑንም የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ገልጿል።

የምክር ቤቱ መግለጫ የታጠቁ አካላት ያላቸውን በስምም ሆነ በትክክል በቦታ ያልጠቀሰ ሲሆን “ጽንፈኛ የፖለቲካ አመለካከቶች እንዲሁም የተደራጁ የወንጀል እና የዘረፋ ፍላጎቶች በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ናቸው” በማለት መግለጹን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች። መንግስትም እንቅስቃሴያቸውን ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል። 

በአማራ ክልል በተሰራ የጸጥታ እና ደህንነት መዋቅር ማደራጀት ስራ “የክልሉን መንግሥት አፍርሶ በኃይል ሥልጣን ለመያዝ ያሰበው ኃይል ፍላጎቱን ለማሳካት እንዳይችል ተደርጓል፤ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ የክልሉን መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመታደግ ተችሏል” ሲል የደህንነት ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ በመላ አገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀዬቸው መመለሳቸውን እና ለመመለስ እየተደረገ ስለሚገኝ ጥረት ገልጿል።