April 24, 2024 – Zemedkun Bekele 

የምሥራች ለዐማራውያን…!

“… በራሳቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነቢያት በሆኑት ጎንደሬዎች፣ በአፄ ቴዎድሮስ ልጆች፣ በጀግኖቹና በአርበኞቹ ጋባዥነት ለአንድ ዓላማ ቆመው ሳለ በሓሳብ ልዩነት ከሁለት ጎራ ተከፍለው ቁርሾ ገብቷቸው የነበሩት ጀግኖች ባቀረቡልኝ “የአሸማግለን” ጥሪ መሠረት እኔ ዘመዴ አባ ደፋር አንድ ለእናቱ፣ ሺ ለጠላቱ፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው፣ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ፣ የሐረርጌውን መራታ ጥሪያቸውን ተቀብዬ እንደ መጽሐፍም ቃል “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።” ማቴ 5፥9 ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት የማሸማገል ሥራውን ጀመርኩ።

“…ጎንደሬዎቹን ጆኒ፣ ዘመንና አዱኛን ከጀርባ አሰልፌ፣ የሸዋውን ካህን ከኦሀዮ በጸሎት አስጀምሬ፣ በመጨረሻም ከወሎ የደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ የነበሩትን አባ ጽጌሥላሴን ጨምሬ፣ ገዳማውያን በጸሎት እንዲያግዙን ፈቃደ እግዚአብሔርንም ጠይቀን ስናበቃ ወደ ውይይቱ ገባን። ውይይቱ ሲጀመር ከባድ ነበር። ውሎ ሲያድር እየቀለለ መጥቶ ዛሬ ሚያዚያ 16/2016 ዓም እግዚአብሔር ከብሮ ሰይጣን ዲያብሎስም አፍሮ፣ በእለተ ኪዳነምህረት በደስታ፣ በእንባ፣ በፍቅር የሽምግልናውን ሂደት በይቅርታ ተፈጸመ።

“…አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የጎንደር ዕዝ የበላይ ጠባቂ፣ አርበኛ ባዬ ቀናው የዐማራ ፋኖ በጎንደር ሰብሳቢ፣ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ መሪ፣ ኮ/ል ታደሰ የዐማራ ፋኖ በጎንደር የጦር አዛዥ በተለይ አርበኛ ፋኖ ደረጀ ሁላችንንም አስለቅሶን ሁላቸውም ታርቀው፣ ይቅር ተባብለው፣ የደስታ ጥይት ተተኩሶ፣ የተራራቁት ተቀራርበው በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ የተዋሐደ አመራር መርጠው በአንድ የጎንደር ፋኖ ሊገለጡ ወስነው ይሄንኑ ለመላው ዐማራ ንገር ብለው አዘውኝ ነገሩ ተቋጭቷል።

• እግዚአብሔር ይመስገን

ዘመድኩን በቀለ (መምህር)

Image