በናይሮቢ መዲና በጣለ ከፍተኛ ዝናብ መንደሮች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል
የምስሉ መግለጫ,በናይሮቢ መዲና በጣለ ከፍተኛ ዝናብ መንደሮች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል

ከ 3 ሰአት በፊት

በኬንያ መዲና ናይሮቢ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ መንገዶች በውሃ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣን የጎርፉ መጠን “እጅግ በከፋ ደረጃ እየጨመረ ነው” ብለዋል።

ባለፉት ቀናት በኬንያ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ መጠነ ሰፊ ውድመት እያስከተለ ነው።

የመንግስታቱ ድርጅት ቢያንስ 32 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና ከ40 ሺህ የሚበልጡት ደግሞ በዝናቡ እና ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለመሸሽ መገደዳቸውን ገልጿል።

በኬንያ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት የናይሮቢ ተወካይ የሆኑት ኤዲን ሲፉና ባጋሩት ቪዲዮ በጎርፍ የተጥለቀለቀ ሰፈርን አስመልክተዋል።

በቪዲዮው ላይ መውጫ ያጡ ነዋሪዎች የቤታቸው ጣሪያ ላይ ተቀምጠው ይታያሉ። “በናይሮቢ ያለው ሁኔታ እጅግ በከፋ ሁኔታ እየተባባሰ ነው። የከተማው መንግሥት ከአቅሙ በላይ ሆኖበታል። ሁሉም ሀገር አቀፍ የአደጋ ጊዜ ደጋፊዎችን እንፈልጋለን” ብለዋል።

በናይሮቢ መዲና በጣለ ከፍተኛ ዝናብ መንደሮች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል

በናይሮቢና አካባቢው በርካታ የመኖሪያ መንደሮች በአንድ ለሊት በሚጥል ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጥለቀለቁ ይገኛሉ።

ማታሬ በተባለ ከፍተኛ ሰዎች በሚኖረበት አከባቢ ነዋሪዎች ጣሪያ ላይ ለማደር መገደዳቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የሀገሪቱ ዋና ዋና መንገዶች ከፍተኛ መጠን ባለው ዝናብ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን የትራፊክ መጨናነቅን እያስከተሉ ነው።

የኡበር አሽከርካሪ የሆነው ኬልቪን ሙዋንጊ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ሲናገር “ከተማዋ ቀጥ ብላለች። ምክንያቱም አብዛኞቹ መንገዶች በጎርፍ ተሞልቷል።”

ባለፈው ምክሰኞ በሁሉም አቅጣጫ ባለ ጎርፍ ምክንያት መውጫ ያጣን የአምሰት አመት ታዳጊ በደቡባዊ ናይሮቢ ያታ በተባለ ስፍራ ፖሊስ በሂሊኮፕተር በመታገዝ ታድጎታል።
የምስሉ መግለጫ,በጎርፍ ምክንያት መውጫ ያጣን የአምሰት አመት ታዳጊ በደቡባዊ ፖሊስ በሂሊኮፕተር በመታገዝ ታድጎታል

ባለፈው ምክሰኞ በሁሉም አቅጣጫ ባለ ጎርፍ ምክንያት መውጫ ያጣን የአምስት አመት ታዳጊ በደቡባዊ ናይሮቢ ያታ በተባለ ስፍራ ፖሊስ በሄሊኮፕተር በመታገዝ ታድጎታል።

የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር “ለረዥም ሰዓታት መውጫ ያጣው ህጻኑ በሚታይ ሁኔታ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ይንቀጠቀጥ ነበር። ደህንነቱ ተጠብቆ ከአደጋው ተርፎ አቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስዷል” ብሏል።

ኬንያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም ባለፉት ሳምንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀዋል።

በብሩንዲ 100 ሺህ ሰዎች በጎርፍ ምክንያት ሲፈናቀሉ በታንዛንያ ደግሞ 58 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ1997 እና 1998 በምስራቅ አፍሪካ በተመሳሳይ በተከታታይ የጣለው ከባድ ዝናብ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በቀጠናው ባሉ አምስት ሀገራት 6 ሺህ ሰዎች በጎርፍ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸው ተዘግቦ ነበር።