April 25, 2024 – Konjit Sitotaw 

ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተገለጸ

ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ “እብደት በሕብረት” የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ “እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ” እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል።

ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና “በመልካም” ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል።

በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።

እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር ‘ቧለቲካ’ የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም።