
Fikre Tolossa
ሩዋንዳ የተመሰረተችው ሩዋንዳ በተባለ የአጼ ሰርጸ ድንግል ብርጌድ ነው።
**************†************************፣*
በመሪራስ አማን በላይ የተደረሰው የጥንቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ መጽሀፍ ውስጥ
ገጽ 228 ላይ አጼ ሰርጸ ድንግል የዛሬ 500 ዓመት ገደማ ከሸዋ ተነስተው ጁባ ሱዳን ወርደው ነበር። ከዛ ወድ ዛንዚባር ታንዛኒያ ሄደው ከዩጋንዳ በታች እና ከታንዛንያ ጎን ዛሬ ሩዋንዳ በሚባለው ያኔ ሌላ ስም በነበረው ቦታ ላይ ሩዋንዳ የተባለ 4000 የጦር ሰራዊታቸውን ራቁታቸውን የነበሩትን ጎሳዎሽ (ሁቱዎችን?) ልብስ መልበስ እንዲያስተምሩና እንዲያሰለጥኑ፣ ,እንዲሁም አገር እንዲያቀኑ እንደአሰፈሯቸው ይገልጻል።
እንግዲህ ዛሬ ቱትሲ የተባሉት እና ሌሎቹም እኛን ኢትዮጵያውያንን የሚመስሉት ሩዋንዳኖች እና ብሩንዲዎች የተገኙት ድብልቅልቅ የኢትዮጵያ ጎሳዎች ከነበሩበት ሩዋንዳ ከተባለው አራት ሺ የጦርሰራዊት ብርጌድ ነው ማለት ነው። የእዚህም ምስክሩ የሩዋንዳኖቹ መልክ እኛን መምሰሉ ነው።
ሁቱ የሚባሉት ነገዶች ደግሞ ነባር የሀገሩ ኗሪዎች ናቸው። ቱትሲ የሚባሉት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእነሱ አይጋቡም። በእዚህም ምክንያት ኢትዮጵያዊ ገጥታቸውን ለመጠበቅ ችለዋል። ሁቱዎች እንደወራሪ እያዩ ስለሚጠሏቸው ጨፍጭፈዋቸው እንደነበር የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው። በሚጨፈጭፋቸው ጊዜ ወደሀገራችሁ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ እያሉ ነበር።
እዚህ እታች የሰፈረችው ልጅ ቁርጥ ኢትዮጽያዊ መሆኗን ምስል ያረጋግጣል። ደማችንም ይነግረናል።

