
ከ 1 ሰአት በፊት
በርካታ ፍልስጤምን የሚደግፉ የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተቃውሟቸው ቀጥለው የአካዳሚክ ሕንጻውን መቆጣጠራቸው ተገለጸ።
የጋዛን ጦርነት በመቃወም በኒው ዮርክ ዩኒቨርስቲ ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ሀሚልተን የተባለውን ሕንጻ ተቆጣጥረዋል።
በሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ተቃውሞዎችን ያቀጣጠለውን የተማሪዎች ተቃውሞ ለማስቆም የዩኒቨርስቲው አመራሮች ቢሞክሩም አልተሳካም።
አንድ ተማሪ ዩኒቨርስቲው “ሕግ አልባ ሆኗል” ስትል ገልጻለች።
ተማሪዎች እና ሠራተኞች ከዩኒቨርስቲው እንዲርቁ ተነግሯቸዋል።
ሰኞ ተቃውሞውን እንዲያቆሙ ቀነ ገደብ ዩኒቨርሰቲው የሰጣቸው ቢሆንም በተቃውሞ በመቀጠላቸው ተማሪዎችን እያገደ ይገኛል።
ቀነ ገደቡ ቢያልፍም ተማሪዎቹ ተቃውሞን ገፍተውበታል።
‘ኮሎምቢያ ስቱደንትስ ፎር ጀስቲስ ኢን ፓለስታይን’ የተባለው ዋነኛው የተቃውሞው አቀጣጣይ በኤክስ ገጹ፣ የመብት ተሟጋቾች ለቅጥር ጊቢው ጥበቃ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
ሀሚልተን ሕንጻን በቁጥጥራቸው ሥር ማዋላቸውን ይኸው ስብስብ ገልጿል። ይህ ሕንጻ እአአ በ1968 የተማሪዎች ተቃውሞ ማዕከል ነበር።
‘ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ አፓርታይድ ዳይቨስት’ የተባለው የተማሪዎች ስብስብ እንዳለው፣ ሕንጻውን የተቆጣጠሩት ጋዛ ውስጥ ተገድላ በተገኘችው የስድስት ዓመቷ ሂንድ ራጃብ ስም ነው።
ተቃዋሚዎች የሕንጻውን መስኮት ሰብረው እንደገቡና በሩን በመዝጋት ወደ ሕንጻው መንገድ እንደዘጉ የገለጸችው አንድ ተማሪ እንዳለችው “ሙሉ በመሉ ሕግ አልባለት ሰፍኗል”።
ባለፉት ሳምንታት የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በተቃውሞ እየተናጡ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ታስረዋል። ከታሰሩት መካከል የቴክሳስ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ኃላፊ ቮልከር ቱርክ፣ አንዳንድ የፀጥታ ባልደረቦች እርምጃዎች “ያልተመጣጠኑ ናቸው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
“ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት የማኅበረሰብ ማዕዘን ነው” ሲሉ አክለዋል።
- የቢቢሲ ጋዜጠኛ አሳዛኝ የጋዛ ገጠመኞችከ 9 ሰአት በፊት
- የአብን አባሉ አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከአማራ ክልል የመንግሥት ኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁከ 4 ሰአት በፊት
- በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ ሲታወሱከ 2 ሰአት በፊት
በቨርጂኒያ ኮመንዌልዝ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን ገልጸዋል።
ፖሊስ ተማሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ “በተደጋጋሚ” መግለጹን አስታውቋል።
ከተቃውሞው ተሳታፊዎች አብዛኞች ተማሪዎች አይደሉም ሲልም ከሷል።
በኤቨንስተን እና ኤለኖይስ ተማሪዎች ለቀናት በተቃውሞ ቀጥለዋል። “ሰላማዊ ተቃውሞን” እንደሚፈቅድ ዩኒቨርስቲው ተናግሯል።
የመብት ተሟጋቾች ወደ እስራኤል የሚላክ ገንዘብ እንዲቆም ዩኒቨርስቲዎቻቸውን እየጠየቁ ነው።

የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እርምጃ እንዲወስድ ጫናው በርትቷል።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ማይክ ጆንሰን “እየሆነ ያለው አሳፋሪ ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን ድጋፍ እና የጋዛን ጦርነት በተመለከተ የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ዋነኛ የውይይት መድረክ ሆኗል።
ዴሞክራቶች የዩኒቨርስቲው አመራር “ቁርጠኛ አቋም መውሰድ ካልቻለና የሁሉንም ተማሪዎች ደኅንነት የማያስጠብቅ ካልሆነ እንዲለቅ” ጠይቀዋል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሚኖውች ሻፊክ እንዳሉት፣ ዩኒቨርስቲው ወደ እስራኤል ከሚላከው ላይ የሚቀንሰው አይኖርም።
ከተማሪዎች ጋር እስካሁን የተደረጉ ንግግሮች እምብዛም ለውጥ አላሳዩም።

ተማሪዎቹ የተሰጣቸው ቀነ ገደብ ሲያልቅ ነው ዩኒቨርስቲው እንደሚያግዳቸው የገለጸው። ዕገዳው ከተጣለ መመረቅ አይችሉም ማለት ነው።
ተቃውሞ የሚያሰሙ ተማሪዎች ቅጣት እንዳይጣልባቸውም ተማሪዎቹ ጠይቀዋል።
ከዩኒቨርስቲው አመራሮች ጋር እየተደራደሩ ካሉት ተማሪዎች አንዱ የሆነው ማሕሙድ ካሕሊል ለቢቢሲ እንደገለጸው፣ በድጋሚ ፖሊስ ሊጠራባቸው ይችላል።
ሶርያ ያደገው ፍልስጤማዊ ስደተኛ ማሕሙድ “ተማሪዎቹ አሉ። ድምጻቸውን ማሰማት ቀጥለዋል” ብሏል።
ተማሪዎቹ ሊደርስባቸው የሚችለውን በመፍራት ፊታቸውን መሸፈኛ ማስክ አድርገው ይታያሉ።
ቢያንስ በ22 የአሜሪካ ግዛቶችና ዋሽንግተን ዲሲ ተቃውሞዎች እንዳሉ ቢቢሲ ተረድቷል። በካናዳ፣ በፈረንሳይና በአውስትራሊያም ተቃውሞዎች ሪፖርት ተደርገዋል።
አይሑዳውያን ተማሪዎች ለደኅንነታቸው እንደሚሰጉ ሲገልጹ ተደምጧል።
የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሪን ጄን-ፒሬ “ነገሩ አሳዛኝ እንደሆነ ይገባናል። ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሕግ መከተል አለበት” ብለዋል።