May 1, 2024 – Konjit Sitotaw 

ኢትዮጵያ፣ በወጪና ገቢ ንግድ መስኮች የጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን ለውጭ ኩባንያዎች ለመክፈት መወስኗ ለኬንያ ኩባንያዎች ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል።

ገበያቸውን ለማስፋት ከሚፈልጉት ግዙፎቹ የኬንያ ኩባንያዎች መካከል፣ ናይቫስ እና ኩይክ ማርት የተባሉት ሱፐርማርኬቶች እንደሚገኙበት ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባደረገው አዲስ ማሻሻያ፣ በችርቻሮ እና ጅምላ ንግድ ለሚሠማሩ ኩባንያዎች የመነሻ ካፒታል መጠንና የቅርንጫፎችን ብዛትን ጨምሮ ጠበቅ ያሉ መስፈርቶችን አስቀምጧል።