May 1, 2024 

“የዓለም ባንክ የአፍሪካ ሀገራትን መዋቅራዊ ችግሮች ከመደገፍ ለሴሚናር ገንዘብ ማውጣት ይቀለዋል” የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የዓለም ባንክ ድሃ የአፍሪካ ሀገራት ለዕድገታቸው እንቅፋት የሆኑ የእርሻ፣ ትራንስፖርትና መሰል መዋቅራዊ ችግሮችን እንዲፈቱ ብድር ከመስጠት ይልቅ ለሚዘጋጁት ‘ሴሚናሮች’ ብድር ቅድሚያ ይሰጣል ሲሉ ወቀሳ ሰነዘሩ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በኬኔያ በተካሄደው የአለም አቀፍ ልማት ማህበር የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ነው። ” አለም ባንክ ሰዎች ተቀምጠው ለሚመገቡት ሴሚናሮች  ብድር ለመስጠት ፈጣን ናቸው። ነው ነገር ግን የመስኖ እና የመሠረተ ልማት ልማትን አይደግፉም ” ሲሉ ወቅሰዋል።

ፕሬዝዳንቱ አፍሪካ ዘላቂ ልማት (Sustainable underdevelopment) አያስፈልጋትም አፍሪካ የምትፈልገው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ (Socio-Economic Transformation) ነው ያሉ ሲሆን ዘላቂ ልማትን የሚባለውን ፅንሰ ሀሳብ እድገት የሌለው ሲሉ ገልጸውታል።

“አንድ ሴት በዚህ ዓመት ካረገዘች በሚቀጥሉት ሦስት እና አራት ዓመታት እርጉዝ አትሆንም፥ ይህ ፈጽሞ አይፈጠርም ተፈጥሯዊው እድገት ለወራት ታረግዛለች ልጁ ያድጋል፤ ይወለዳል፤ ይጎለምሳል። የሆነ ምዕራፍ ላይ እርግዝናው (Quantitative) ወደ ልጅነት ይቀየራል (Qualitative) እነዚህን ቃላት በዶክመንታችሁ አስተካክሏቸው።” ሲሉ ገልጸዋል።

ፕሬዚደንት ሙሴቬኒ አክለውም፥ አፍሪቃ የጥሬ ዕቃዎቿን ወደ ውጭ መላክ እንድታቆም የጠየቁ ሲሆን ጥሬ እቃ ላይ እሴት ሳይጨመር መላክ በአፍሪካዊያን ሀብት ሌሎችን ማበልጸግ እንደሆነ የቡና እና የማዕድን ሀብትን በምሳሌ አንስተው አስረድተዋል።

“ኡጋንዳ ሀብታም ሀገር ብትሆንም አብዛኞቹ ዜጎቿ ለዕለት ጉርስ እንጂ ለኪስ የሚሆን ገንዘብ ከሚያገኙበትን ሥርዓት ( Money Economy) ውጪ ናቸው። ይህንን ለመቅረፍ ገንዘብ የሚሰጠኝ የለም ምክንያቱም ሁሉም ገንዘብ ለአቅም ማጎልበቻ (Capacity Building ) ነው። እኛ ግን በራሳችን ፈንድ እየሰራን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

በአፍሪካ የግሉ ዘርፍ እየተደገፈ ባለመሆኑ እድገት እየተመዘገበ እንዳልሆነ የገለፁት ሙሴቬኒ የግሉ ዘርፍ እንዲበረታታ በቅድሚያ በአነስተኛ ዋጋ ማምረት መቻል ለዚህም ደግሞ  የመንገድ የኤሌክትሪክ ሀይል ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅሰው የዓለም ባንክ ለእነዚህ ነገሮች ፈንድ ያደረገበትን ኦዲት ያድርግ ሲሉ ጠቅሰዋል።