May 1, 2024 

“ ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛው ሊቋቋመው አልቻለም ” – አቶ ካሳሁን ፎሎ

ዛሬ የሜይዴይ በዓል እየተከበረ ነው።

በዓሉ አስመልክቶ ትላንት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ተገኝቶ ነበር።

ኮንፌዴሬሽኑ ፤ በባለፈው ዓመት በተከለከለው ሰልፍ ሳቢያ ከመንግሥት ጋር የገጠማችሁ አለመግባባት ተፈታ ? የሠራተኞች ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ አሁንስ ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል።

የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ “ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው ክልከላው ደርሶን የነበረው። በመነጋገር መፍታት አልቻልንም በወቅቱ ” ብለዋል።

“ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደተከለከልን ከመንግሥት አካላት ጋር በየደረጃው ተወያይተናል። ክልከላው ሆን ተብሎ ሠራተኛው ያለውን ጥያቄ እንዳያቀርብ የተደረገ እንዳልነበር ተግባብተናል ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ከዚያም ጥያቄያችንን አደራጅተን ለጠ / ሚኒስትሩ አቅርበን ግብር እንዲቀነስ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ስኬል እንዲወሰን መጠየቃችን ይታወቃል። ጠ/ሚኒስትሩ በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ እንደሚሰጥ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ያኔ ” ሲሉ አስታውሰዋል።

“ አቅጣጫ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች እየተከታተልን ነው ” ያሉት አቶ ካሳሁን ፣ “ ነገር ግን አቅጣጫ የተሰጠባቸው የኑሮ ውድነቱን የተመለከቱ ጥያቄዎች ምላሽ አሁንም ዘግይቷል። ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛውም ሊቋቋመው አልቻለም ” ብለዋል።

አሁን ምን አዲስ ነገር አለ ? ለሚለው ፦

➡️ ከሠራተኛው በነጻ መደራጀት ጋር በተያያዘ ለሁሉት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው መንግስትና ሠራተኛ ቁጭ ብለው የሚወያዩበት የአሰሪና ሠራተኛ አማካሪ ቦርድ ዘንድሮ ሥራ ጀምሯል፡

➡️ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሁሉም ክልሎች ሠራተኛ እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች በሚገኙበት ስብሰባ ግምገማ ማካሄድ ተጀምሯል ጥያቄዎች በዚሁ አካሄድ ይፈታሉ ሲሉ አስረድተዋል።