የብሪታንያው ሃስኪ የተባለ ታክቲካል ድጋፍ ሰጪ መኪና

ከ 3 ሰአት በፊት

የሶቪየት ህብረት ናዚ ጀርመንን ማሸነፍ አስመልክቶ በሞስኮ ግዙፍ የድሉ መታሰቢያ ፓርክ ይገኛል። ቦታው አሁን አዲስ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሆኗል።

ኤግዚቢሽኑ ግን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።

ለዕይታ የቀረቡት ዩክሬን ውስጥ በሩሲያ ጦር የተያዙ የምዕራባውያን ወታደራዊ መሣሪያዎች ናቸው።

መሣሪያዎቹ የጦርነቱ ዋንጫዎቿ ሲሆኑ አደባባይ ላይ ለዕይታ አብቅታ ጡንቻዬን ተመልከቱልን ብላለች።

ከተማረኩት መካከል ለዩክሬን የተበረከተው የብሪታንያው ሃስኪ የተባለ ታክቲካል ድጋፍ ሰጪ መኪና ይገኝበታል። የፊት መስታወቱ በጥይት ተበሳስቶ ቀርቧል።

ከሃስኪ ጎን ደግሞ ለዩክሬን ጦር የተሰጡ የምዕራባውያን ታንኮች ተቀምጠዋል። በጦር ሜዳ ጉዳት የደረሰበት የአሜሪካው አብራም የተሰኘ ታንክ ቆሟል። የጀርመኑ ሊዮፓርድ የተሰኘ ታንክም ተገኝቷል።

በርካታ ቁጥር ያላቸው የጀርመን የጦር መሣሪያዎችም አሉ። “ታሪክ ራሱን እየደገመ ነው” የሚል ጽሑፍም ሰፍሮበታል።

አሜሪካ ያመረተችው አብረሃም የተሰኘው ታንክ

ህዝቡ በዩክሬን እና በሁለተኛው የአለም ጦርነት አንድ ዓይነት መሆኑን እንዲያስብ የሩስያ ባለስልጣናት ይፈልጋሉ። ይህም ሩሲያ በውጭ ጠላቶች ተጠቂ እንደሆነች ማሳየትን ነው ዓላማቸው።

እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሁለቱ ጦርነቶች በጣም የተለያዩ ናቸው። በ1941 ጀርመን ሩሲያን ወረረች። በ2022 ደግሞ ሩሲያ ዩክሬን ላይ ወረራ ፈጽማለች።

የጦርነት ኤግዚቢሽኑ በሰዎች ተሞልቷል።

ሩሲያውያን ወታደራዊ መሣሪያዎቹን እየተመለከቱ በዝግጅቱ እየተዝናኑ ነበር።

ከባለቤቷ እና ከሴት ልጇ ጋር የተገኘችው ናታሊያ “ይህ የማይታመን ነው። እጅን በአፍ የሚያስጭን ነው” ብላለች።

“ወታደሮቻችን እነዚህን ዋንጫዎች ማግኘት ችለዋል ብሎ ማሰቡ አስገራሚ ነው።”

ከ30 በላይ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

በርካታ ሰው የጦር መሣሪያዎቹን እየጎበኘ ነው

ግን ለምን?

ሩሲያውያን መሣሪያዎቹን አላመረቷቸውም። ቀደም ሲል በዩክሬን ጦር የተማረኩትን የሩሲያ ወታደራዊ መሣሪያዎች ኪዬቭ ለዕይታ አብቅታለች።

ይህ ኤግዚቢሽን ለሩሲያ ባለስልጣናት በርካታ ቁልፍ ዓላማዎች አሉት።

የመጀመሪያው ዩክሬን፣ ናቶ (በአጠቃላይ በምዕራቡ ዓለም) በሩሲያ ላይ ጦርነት እየከፈቱ ነው ሚለውን የክሬምሊን ተረክ የማጠናከር ነው። ዓላማውም በሩዲያውያን አእምሮ ውስጥ ምዕራባውያንን አጋንንት አድርጎ የመሳል ነው።

እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ዩክሬንን የወረረችው ሩሲያ ናት። ምዕራባውያን መሪዎች ሞስኮ አስጠንቅቀው ነበር።

ሩሲያ አሁንም “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” የምትለውን ለመጀመረችው በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የግል ውሳኔ ነበር።

ምዕራባውያን የጦር መሳሪያ ይዘው ኪዬቭ መከላከል ያዙ። ዓላማውም ከሩሲያ ባለሥልጣናት በተቃራኒ ሩሲያን ለማጥፋት አይደለም።

ታሪካዊ ተምሳሌታዊነትም አለው።

የድል ፓርክ ሂትልር የተሸነፈበትን መጪውን የድል ቀን የሚያከብርበት ብሔራዊ በዓልን የሚዘክሩ ቀይ ባንዲራዎችን እየተውለበለቡበት ነው።

የሩሲያ ዋነኛ መልዕክት ከጦር መሣሪኣዎቹ ጎን በትልቁ ሰፍሯል።

“ድላችን የማይቀር ነው።”