
2 ግንቦት 2024, 18:32 EAT
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኬንያ ታሪክ የመጀመርያዋን ሴት የአየር አዛዥ ሾሙ።
ሜጀር ጄኔራል ፋጡማ ጋይቲ አሕመድ በከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጣን ለመሾም በኬንያ ታሪክ የመጀመርያ ሴት ናቸው።
ጄኔራል ቻርለስ ካሃሪሪ በቅርቡ በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸውን ባጡት የጦር አዛዥ ቦታ ተተክተዋል።
ሜጀር ጄኔራል ፋጢማ በኬንያ ታሪክ ብርጋዲየር ጄኔራልና ሜጀር ጄኔራል ማእረግ ለማግኘትም የመጀመርያዋ ሴት ናቸው።
ሜጀር ጄኔራል ፋጢማ የኬንያ መከላከያን የተቀላቀሉት በፈረንጆቹ 1983 ሲሆን ያን ጊዜ የሴቶች ብቻ የሆነውን ዊመን ሰርቪስ ኮርፕስ የተባለውን ኃይል ተቀላቅለው ነበር።
ይህ የሴቶች ኮርፕስ ለዋናው መከላከያ አስተዳደራዊና የሎጂስቲክ እንዲሁም የሕክምና ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት ነበር የተሰጠው።
- የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት ፈቀደ2 ግንቦት 2024
- ሩሲያ ከዩክሬን የማረከቻቸውን የጦር መሣሪያዎች ለዕይታ አበቃች2 ግንቦት 2024
- የጋዛን ጦርነት የተቃወሙት የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ መወረራቸው እንዳሳዘናቸው ገለጹ2 ግንቦት 2024
በፈረንጆቹ 1999 ይህ ኃይል እንዲፈርስ ሲደረግ አባላቱ በኬንያ አየር፣ ምድርና ባሕር ኃይል እንዲቀላቀሉ ለመጀመርያ ጊዜ ተፈቀደላቸው።
የሜጀር ጄኔራል በዚህ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጣን ላይ መሾም በኬንያ የጾታ እኩልነት ላይ ትልቅ እምርታዊ ትርጉም አለው ተብሏል።
በ2018 በፈረንጆቹ ፋጢማ ወደ ሜጀር ጄኔራልነት የተሾሙት በያነው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ነበር።
በወቅቱ ኡሁሩ ኬንያታ “እተማመንብሻለሁ፤ ለሴቶች ጥሩ አርአያ እንደምትሆኚ” የሚል ንግግር አድርገው ነበር።
“ሴትም ያለመችበት መድረስ እንደምትችል አሳያቸው ” ብለው ነበር ኡሁሩ በያኔው የሹመት ንግግራቸው።
ሜጀር ጄኔራል ፋጢማ ወደ ውትደርና የገቡት በአጎታቸው ሥነ ምግባርና የውትደርና ዲሲፕሊን ተማርከው እንደሆነ ከዚህ ቀደም ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ይሁንና ጦሩን ለመቀላቀል በወሰኑ ጊዜ የቤተሰብ አባሎቻቸው “አንቺ ሴት ነሽ አርፈሽ ተቀመጭ” ይሏቸው እንደነበር ተናግረዋል።