May 2, 2024 

የማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ኃላፊዎች ከመኖሪያ ቤታቸው በፀጥታ አካላት ታፍነው ተወሰዱ !

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን “ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ” ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ማህበረ ቅዱሳን ሚዲያ ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም።