
ከ 2 ሰአት በፊት
የኬንያ መንግሥት እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በ178 ግድቦች እና የውሃ ማቆሪያዎች (reservoirs) አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
በኬንያ የውሃ አካላት ከመጠን በላይ ስለሞሉ ወይም ሊሞሉ በመቃረባቸው ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሆኑ አስጠንቅቋል።
ከውሃ አካላት አቅራቢያ የሚኖሩ በመላው ኬንያ የሚገኙ እና ከናይሮቢ ወንዝ 30 ሜትር ርቀት ላይ ኑሯቸውን የመሰረቱ ዜጎች ከትላንት ሀሙስ ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ አካባቢያቸውን እንዲለቁ ታዘዋል።
ባለፉት ቀናት እየጣለ ያለው ከፍተኛ ዝናብ በኬንያ እና ታንዛንያ ከባድ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት እያስከተለ ነው።
እንደ ኬንያ ባለስልጣናት መረጃ ከሆነ ከየካቲት ጀምሮ በኬንያ በዚሁ ሳቢያ 188 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 90 ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው ጠፍቷል። በታንዛንያ ደግሞ 155 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ከናይሮቢ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ አካባቢ በእንቅልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገምቷል።
በኬንያ ያለው የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ቀናት ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።
በተለይ የባህር ዳርቻዎች ላይ የባህር እንቅስቃሴዎችን ሊያስተጓጉል የሚችል ከባድ አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ እንደሚጥል የፕሬዝዳንት ሩቶ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የኬንያ ሚትሪዮሎጂ መስሪያ ቤት በሚጥለው ዝናብ እና ንፋስ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጎዱ አካባቢዎቹ አንዱ ናይሮቢ ከተማ እንደሆነ ገልጿል።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ መሬት በከፍተኛ ሁኔታ በውሃ እየተሸረሸረ እንደሆነ ጠቅሷል።
- በመስቀል ላይ የሚፈጸም ስቅላት እንዴት እና የት ተጀመረ?ከ 5 ሰአት በፊት
- እስራኤል በዌስት ባንክ በአንድ ሕጻን ላይ የፈጸመችው ግድያ የጦር ወንጀል ሊኾን እንደሚችል የቢቢሲ ምርመራ አመላከተከ 5 ሰአት በፊት
- የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት ፈቀደ2 ግንቦት 2024
ሚኒስቴሩ ከውሃማ አካላት ነዋሪዎችን የማስወጣት ተግባሩ ምሽት ላይ ሳይሆን አርብ ጠዋት እንደሚጀምር ገልጿል።
ጨምሮ ከእነዚህ አካባቢዎች ለሚወጡ ዜጎች ጊዜያዊ መጠለያ እና ምግብ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
ሆኖም በዚህ ትዕዛዝ ምክንያት ምን ያህል ሰዎች ከአካባቢያቸው እንደሚለቁ የተጠቀሰ ቁጥር የለም።
የኬንያ መንግስት ለጎርፍ እየሰጠ ያለው ምላሽ አነስተኛ ነው በሚል ትችት እየቀረበት ነው።
ሆኖም ፕሬዝዳንት ሩቶ ቢቢሲ ላይ ቀረበው ተገቢውን ስራ እያከናወንን ነው ሲሉ መንግስታቸውን ተከላክለዋል።
ትላንት ከተደረገ የካቢኔ ስብሰባ በኋላ በጎርፉ የተጠቁ ሰዎች እየተደረገላቸው ያለው የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ እየጨመረ እንደሆነ ተገልጿል።