እስራኤል በጋዛ የጀመረችው ጦርነት ለመከፈቱ አንድ ሳምንት ተገናኝተው ነበር አስቀድሞ ኔተናኒያሁ እና ኤርዶአን
የምስሉ መግለጫ,እስራኤል በጋዛ የጀመረችው ጦርነት ለመከፈቱ አንድ ሳምንት ተገናኝተው ነበር አስቀድሞ ኔተናኒያሁ እና ኤርዶአን ተገናኝተው ነበር

3 ግንቦት 2024, 08:03 EAT

ተሻሽሏል ከ 4 ሰአት በፊት

እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለው የማያባራ ጥቃት “እጅግ እየከፋ እና የሰብአዊ ሰቆቃ ማስከተሉን” በመጥቀስ ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ሁሉን የንግድ ግንኙነቶች አቋረጠች።

እስራኤል “ያልተስተጓጎለ እና በቂ የእርዳታ ፍሰትን” ወደ ጋዛ እንዲገባ ካልፈቀደች በስተቀር ይህ ውሳኔ

ጸንቶ እንደሚቆይ የቱርክ የንግድ ሚኒስትር አስታውቋል።

በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ወደ መጠን 7 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል።

የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የቱርኩን ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እንደ “አምባገንን” የሚሰሩ ሲሉ ተችተዋል።

ሚኒስትሩ እስራኤል ካታዝ በኤክስ ገጻቸው ኤርዶጋን የቱርክን ህዝብ እና ባለሀብቶች ጥቅም ከግምት አላስገቡም እንዲሁም ዓለም አቀፍ የንግድ ስምምነትን ችላ ብለዋል ሲሉ ወቅሰዋቸዋል።

ጨምሮም በቱርክ የንግድ ልውውጥ ቦታ ላይ ሌላ አማራጭ እንዲተገበር ማዘዛቸውን ጠቁመዋል። ይህም የሀገር ውስጥ ምርቶችን መጠቀም እና ሌሎች አማራጭ ሀገራትን መፈለግን እንደሚያካትት አንስተዋል።

የቱርክ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እገዳው ሁሉንም ምርቶች እንደሚመለከት ጠቅሷል።

“እስራኤል ያልተስጓጎለ እና በቂ የእርዳታ ፍሰት እስካልፈቀደች ድረስ ቱርክ ይህንን አዲስ ውሳኔ ያለማመንታት እና በቁርጠኝነት ትተገብረዋለች” ሲልም አክሏል።

በአውሮፓውያኑ 1949 ቱርክ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ በርካታ የሙስሊም አማኞች ያሉባትሀገር ነበረች። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ እየሻከረ እየሄደ ነው።

በአውሮፓውያኑ 2010 ቱርክ 10 ፍልስጤምን የሚደግፉ ተሟጋቾች የሆኑ ዜጎቿ በቱርክ ባለቤትነት በተያዘ መርከብ አማካኝነት የእስራኤልን የባህር ላይ የዘጋችውን የጋዛ ሰርጥ መተላለፊያ ለመስበር ሲሞክሩ ከተገደሉ በኋላ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣለች።

በ2016 ግን የሀገራቱ ግንኙነት ዳግም ታድሷል። ሆኖም ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በጋዛ እና እስራኤል ድንበር አቅራቢያ በነበረ ተቃውሞ የተሳተፉ ፍልስጤማውያን ከተገደሉ በኋላ ግንኙነታቸው ሻክሯል። ይህንን ክስተት ተከትሎ ሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን አባረዋል።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ከወራት በፊት እስራኤል ጋዛ ላይ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረች ወዲህ ከፍተኛ ትችቶችን እስራኤል ላይ ሲሰነዝሩ ነበር።

ባለፈው ጥር ላይ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ እየፈጸሙ ያሉት ጥቃት “ሂትለር ካደረገው የሚተናነስ አይደለም” ሲሉ ተደምጠዋል።

በምላሹ ናታንያሁ “ኩርዶች ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈጸመ ያለው፣ አስተዳደሩን የሚቃወሙ ጋዜጠኞችን በማሰር የዓለም ክብረ ወሰን የያዘው ኤርዶጋን ለእኛ ግብረገብነትን ለመስበክ የመጨረሻው ሰው ነው” ሲሉ ተችተዋቸዋል።

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባለው ሁኔታ እየቀረበባት ያለው ትችት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።