ሰበር ዜና
⨳⨳⨳
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ
⨳⨳⨳
ሰሞኑን በበለሳ መስመር የጠላትን ሐይል እያርበደበደ የሚገኘው መብረቁ ብርጌድ ለበዓሉ የድል ዜና እንካችሁ ብሏል።
እንደምናስታውሰው ከሁለት ቀን በፊት ከዛው ቀጠና በነበረው ጦርነት ድሽቃ ጨምሮ ሌሎች ከባባድ መሳሪያዎችን ከነ ወታደሮቹ የማረከው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው እና በዕዙ ቃል አቀባይ የሚመራው መብረቁ ብርጌድ ዛሬም እልህ አስጨረሻ ውጊያ ሲያደርግ ውሏል።
በውጊያው የነብስ ወከፍ መሳሪያወች የተማረኩ ሲሆን ብዙወች ሙት እና ቁስለኛ ሆነዋል። በመጨረሻም ጠላት የየፈረጠጠ ሲሆን ፋኖዎቹ ሚካኤል ደብር ከተማን መቆጣጠር ችለዋል። በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ በፋኖ ቁጥጥር ትገኛለች።
በፋኖ ከፍተኛ ምት የተናደደው የአገዛዙ ሐይል ንፁሐንን መግደሉን እና ልጃገረዶችን መድፈሩን እንዲሁም መጋዘን እና ሱቅ መዝረፉን እና ማቃጠሉን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ አረመኔ ሰው በላ ቡድን በዛሬ እለትም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ከአካባቢው ፈርጥጧል ሲል የዕዙ ቃል አቀባይ እና የብርጌዱ መሪ ሻለቃ ኮማንዶ ያለው አዱኛ ለሚዲያችን ተናግሯል።
በመጨረሻም ትንሳኤውን በጦርነት በመዋሌ ብዘገይም ለመልካም ምኞት መቸም አይዘገይም እና በዱር በገደል ለምትገኙ የትግል ጓዶቸ፣ ለተከበርከው የአማራ ህዝብ እና ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያን በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴ ነው፤ እንኳን ለብርሐነ-ትንሳኤው አደረሳችሁ ብሏል።
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለአማራ ፋኖ!