
የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ
ሰበር ዜና-የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ
⨳⨳⨳
የማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው ቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ቋራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ። ክፍለጦሩ አዳሩን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ያደረ ሲሆን በመጨረሻም ሶስት ካፖችን መደምሰስ ችሏል።
አሶል አካባቢ የሚገኘ የሚሊሻ እና የፀረ ሽምቅ ካፕ፣ ሽመልእግር መውጫ የሚገኝ የአድማ ብተና ካፕ እና አለሙ በር አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ሐይል ካፕ ሙሉ በሙሉ የተመቱ ሲሆን አድማ ብተና፣ፀረሽምቅ እና ሚሊሻ እጅ የሰጠው እጅ ሰጥቶ የተረፈው ተረሽኖል ያለው የክፍለጦሩ አዛዥ እራሱን የመከላከያ ሐይል ብሎ የሚጠራው ገዳይ ቡድን ከተመታው እና ከተማረከው የተረፈው ካፑን ጥሎ በመፈርጠጥ ወደ ጎረቤት ሐገር ሱዳን ተጠግቷል ብሏል።
በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ በኩል ያለው መስመሩ የተቋረጠበት ሲሆን አልጣሽ ፓርክ ከመግባት እና ወደ ጎረቤት ሐገር ከመሻገር የዘለለ አማራጭ የለውም ብሏል። የነብስ አውጭኙን በከባድ መሳሪያ ከርቀት እየተኮሰ እየፈረጠጠ እንደሚገኝ እና ፋኖም እየተከተለ እያሳደደው እንደሆነ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ለሚዲያችን ተናግሯል።
በተልዕኮው በቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦረ ስር የሚገኙ 100 አለቃ ደጀኔ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድ እየተሳተፋ ይጋኛል ሲል ሻለቃው ተናግሯል።
መረጃው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ነው!
ግንቦት 13/2016 ዓ/ም
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለአማራ ፋኖ!
የአማራ ፋኖ ጎንደር ፅዝ ገፆችን ይከታተሉ።
