
ከ 4 ሰአት በፊት
ቅንጡ ቤቶች የሚገነባው የአሜሪካው ሪል ስቴት ባለቤት የሆነው ግለሰብ ጥልቅ ባሕር ከሚመረምር ሰው ጋር የታይታኒክን ቅሪት ለማጥናት ሊሰርጉ አቅደዋል።
የኦሃዮ ግዛት ነዋሪ የሆነው ቱጃሩ ላሪ ኮነር እና ትሪቶን ሰብማሪንስ የተሰኘ ባሕር ሰርጓጅ አስጎብኚ ድርጅት ያለው ፓትሪክ ላሄይ ናቸው ወደማይደፈረው የባሕር ግዛት ለመሄድ ቆርጠው የተነሱት።
ሁለቱ ግለሰቦች ሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ከባሕር ጠለል በታች 3800 ሜትር ጠልቀው የታይታኒክን ፍርስራሽ ሊያጠኑ አቅደዋል።
ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመቱ ኦሽንጌት የተሰኘው የግል ባሕር ሰርጓጅ አስጎብኚ መርከብ አምስት ሰዎች ይዞ ባሕር ውስጥ ከሰጠመ በኋላ ተጓዦቹ መሞታቸው ይታወሳል።
ከዚህ ጊዜ በኋላ የግል ባሕር ሰርጓጅ አስጎብኚ ድርጅቶች ‘ቢዝነሳቸው’ የተቀዛቀዘ ይመስላል።
የኮነር ኩባንያ ቃል አቀባይ እንዳሉት ሁለቱ ሰዎች ወደ ባሕር ወለል የሚሄዱት የተገነባው ሰርጓሥ መርከብ ጠንካራ መሆኑ ከተመረመረ በኋላ ነው።
ሁለቱ ተጓዦች መች ወደ ታይታኒክ ፍርስራሽ ሊሄዱ እንዳሰቡ የታወቀ ነገር የለም።
ሰዎቹ ሊጓዙበት ያሰቡበት መርከብ ትሪቶን 4000/2 አቢሳል ኤክስፕሎረር ይባላል። 4000 የሚለው ከባሕር ጠለል በታች ምን ያህል ሜትር እንደሚጓዝ የሚጠቁም ነው።
- በመንግሥት እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ ግድያዎች እና ጥቃቶች መበራከታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ28 ግንቦት 2024
- ከ30 ዓመታት ነጻነት በኋላም የቀጠለው የደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ አፓርታይድከ 5 ሰአት በፊት
- ኢራን እና ሳዑዲ አረቢያ የሞት ቅጣትን ተፈጻሚ በማድረግ ቀዳሚ መሆናቸው ተገለጸከ 4 ሰአት በፊት
ባለፈው ዓመት አድራሻው ጠፍቶ ከብዙ ፍለጋ በኋላ ተጓዦቹ መሞታቸው የተሰማው ኦሺንጌት ሰርጓጅ መርከብ ከካርበን ገመድ የተሠራ ሲሆን ከ1300 ሜትር በታች መሄድ አይችልም።
የታይታኒክን ፍርስራሽ ለመጎብኘት እየተጓዙ የነበሩ አምስት ግለሰቦች ሰኔ 2023 ነው ሲጓዙ የነበሩባት ሰርጓጅ መርከብ ባጋጠማት እክል ምክንያት የሞቱት።
የኦሽንጌት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት የ61 ዓመቱ ስቶክተን ራሽ ከሌሎች አራት ተሳፋሪዎች ጋር በአደጋው ምክንያት ሞተዋል። የ48 ዓመቱ ብሪታኒያ-ፓኪስታናዊ እና የ19 ዓመት ወንድ ልጁ እንዲሁም ሌላኛው የ48 ዓመት ብሪታኒያዊ እና የ77 ዓመቱ የቀድሞ የፈረንሳይ ባሕር ኃይል አባል ናቸው በአደጋው የሞቱት።
የኦሽንጌት ኃላፊ የነበሩት ስቶክተን ባሕር ሰርጓጅ መርከቧ ጉዞ ከመጀመሯ በፊት የደኅንነት ሁኔታዋን አላጣሩም ተብለው ይወቀሳሉ። ብዙዎች መርከቧ ወደ ባሕር ወለል የመጓዝ አቅም የላትም የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸው እንደነበርም ይነገራል።
የአሜሪካ እና የካናዳ ባለሥልጣናት በኦሺንጌት ጉዳይ አሁንም ምርመራ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
አሜሪካዊው ቢሊየነር ኮነር “ምንም እንኳ ውቅያኖስ እጅግ ታላቅ ጉልበት ያለው ሥፍራ ቢሆንም በትክክለኛው መንገድ ከሄድን የሚያስደንቅ እና የሚያዝናና ነገር መመልከት እንችላለን የሚለውን ማሳየት እንፈልጋለን” ሲሉ ለዎል ስትሪት ጀርናል ተናግረዋል።
ሁለቱ ተጓዥ በኦሺንጌት አደጋ ሳቢያ የተቀዛቀዘውን የሰርጓጅ መርከብ ጉብኝት ኢንዱስትሪ ማነቃቃት ይፈልጋሉ።
ኦሺንጌት ሥራውን ለጊዜው ያቆመ ሲሆን ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ደግሞ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ መሰረዛው ተሰምቷል።
ትሪቶን ሰብማሪንስ የተሰኘው አጋር መሥራች የሆኑት ፓትሪክ ላሄይ እና ኮነር ከዚህ ቀደም ሲሬና ዲፕ ተብሎ ወደሚታወቀው ማሪያና ትሬንች ወደሚገኘው ጥልቅ ሥፍራ ሄደው ያውቃሉ።
ከባሕር ጠለል በታች 36 ሺህ ጫማ የሚረዝመው ማሪያን ትሬንች የምድራችን ዝቅተኛ ሥፍራ ነው።