May 29, 2024 – Konjit Sitotaw 

ፋኖን በአስር ቀናት ውስጥ አጠፋለሁ እያለ የሚዘምረው የአብይ አህመድ ጦር በአስር ደቂቃ ውስጥ ራሱን አጠፋ። የመከላከያ ልብስ የለበሱ የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎችና የኦሮሚያ ሚሊሻ አባላት የምንጃር ሸንኮራ አካባቢ አማራን ለመውጋት መሰለፋቸው ተረጋገጠ። ጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የነጎድጓድ ክፍለጦር አንበሳው ብርጌድ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሻለቃ በወሰደው አስደናቂ የማጥቃት ኦፕሬሽን ከፍተኛ የጦር አመራሩን ጨምሮ በርካታ የእነ አስታጥቄ ሰራዊቶች እንዳልሆነ ሆነው ተቀጥቅጠዋል።

ግንቦት 18/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:00 እስከ ሌሊቱ 11:00 ድረስ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የነጎድጓድ ክፍለጦር አንበሳው ብርጌድ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሻለቃ ደብረብርሀን ሪጂዮ ፖሊታንት አፄ ዘረ ያዕቆብ ክፍለከተማ አካባቢ የመሸገውን የብርሀኑ ጁላ ጦር ካምፓቸው ላይ በወሰደው የተጠና የማጥቃት አስደማሚ ኦፕሬሽን አዋጊ የጦር አመራሩን ጨምሮ በርካቶች ላይመለሱ የተሸኙ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነው የጦር ካምፓቸውን ለቀው ወደ መሀል ከተማ ፈርጥጠዋል። በተያየዘ ዜና በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌድ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4:30 አካባቢ በወሰደው የተጠና ልዩ የማጥቃት ኦፕሬሽን አስደማሚ ጀብዱን ተጎናፅፏል።

ከያለበት ተሰባስቦ አለኝ ያለውን ሜካናይዝድ የጦር መሳሪያ በመያዝ የምንጃር ሸንኮራና የአካባቢውን ማህበረሰብ ወረራ ወረራ ለመፈፀም እና የአማራን ህዝብ ከምድረገፅ ለማጥፋት ከነብርሀኑ ጁላ ተልዕኮ ተቀብሎ በተለያየ አቅጣጫ በኩል ሲሰባሰብ የነበረው እነ አብይ አህመድ ጥምር ጦር እያሉ የሚቀልዱበት የኦሮሚያ ልዩ ሀይል በተወሰደበት መብረቃዊ ጥቃት የአስከሬን ክምሩን ተሸክሞ ወደመጣበት ፈርጥጦ ተመልሷል።

ፈጣን እና አስደናቂ የቆረጣና የደፈጣ ውጊያ በማድረግ የተካኑት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የከሰም ክፍለጦር በ፲ አለቃ ፍቃዱ ጥላሁን የሚመራው የነበልባል ብርጌድ ፋኖን በአስር ቀን ውስጥ ለማጥፋት አቅዶ የመከላከያ ልብስ በመልበስ የመጣውን ፀረ አማራ የኦሮሚያ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እንደአመጣጡ ተቀብለው አስር ቀን ሳይቆይ በአስር ደቂቃ ብቻ አሰናብተውታል። ለሰዓታት ያህል ባልጪ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በተካሔደው እልህ አስጨራሽ የቆረጣ ውጊያ በርካቶች የአብይ አህመድ መልዕክተኞች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነው ነፍሳቸውን ለማትረፍ ካምፓቸውን ለቀው ፈርጥጠዋል።

ነውረኛው የአብይ አህመድ ጦር ግንቦት 19/2016 ዓ.ም በአውራ ጎዳና በኩል በተለምዶ ቦሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያለምንም ምክንያት ንፁሀን ግለሰቦች ላይ ያነፃፀረ ተኩስ በመክፈት አራት ንፁሀን ግለሰቦችን ገድሏል። በአጠቃላይ ከያለበት በመሰባሰብ ወደ አማራ ክልል እየተመመ የሚገኘው የእነ አብይ አህመድ ፀረ አማራ ቡድን በሸዋ የተለያዩ አካባቢዎችም ተበታትኖ የሞት ሞቱን ቢፈራገጥም የአማራ ፋኖ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑንና ይህ ነውረኛ ወንበዴ ቡድን በአጭር ቀናት ውስጥ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ መላው የአማራን አካባቢ ለቆ እንዲወጣ የአማራ ፋኖ ልዩና የተናበበ ኦፕሬሽኑን ይጀምራል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል