May 29, 2024 

ቀደም ሲል ‹‹የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት›› ይባል የነበረው ተቋም ዛሬ ከፍ ሲል የኦሕዴድ-ብልጽግና ወታደራዊ ክንፍ፤ ዝቅ ሲል የዐቢይ አሕመድ የግል ዙፋን ጠባቂ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ከውጭ ወረራ የሚከላከልላት  ‹‹መከላከያ›› የሌላት አገር ሆናለች፡፡   ዐቢይ አሕመድና የእርሱ ዙፋን ጠባቂ የሆኑ ጀኔራሎቹ በየሚዲያው እየወጡ የሚቀጥፉት ቅጥፈት ኢትዮጵያ መከላከያ የሌላት ሃገር የመሆኗን ሃቅ አይቀይረውም።

1)  ሰራዊቱ ከጦርነት ወደሌላ ጦርነት በመሸጋገሩ ከፍተኛ መሰላቸት አሳይቷል፤

2)  በሰራዊቱ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የዝርፊያ እና ማኀበራዊ ብልግና ፉክክር እንጅ የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ ፉክክር የላቸውም፡፡ ፉክክሩ በዘረፋና በወሲብ ቅሌት ላይ ሆኖ ይታያል፤

3)  የሥልጣን ተረኝነት ስሜቱ በሠራዊቱ ዘንድ የፈጠረው ቅሬታ የውስጥ አርበኞችን ቁጥር ጨምሮታል፤

4)  አገዛዙ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳው ‹‹እየተገነባ ነው›› ቢሉትም ሰራዊቱ አንድነቱን አጥቶ እየተናደ ነው፤

5)  ከሰራዊቱ እየከዳ የሚኮበልለው ቁጥሩ እጅግ ጨምሯል፤

6)  ሰራዊቱ የሚዋጋለት ዓላማ የለውም፤ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰላችቷል፤

7)  ሰራዊቱ በሕዝብ ዘንድ ገዳይና ዘራፊ ተደርጎ ይቆጠራል፤ ከሕዝብ ተነጥሏል፤ 8)  መሬት የታደለው ኮለኔልና መስመራዊ መኮንን መኮብለሉንና ፋኖን መቀላቀሉን ቀጥሏል፤

9)  ኮማንዶ፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ የባሕር ኃይል … ወደ ውጊያ ያልተጣደ ኃይል የለም ነገር ግን ጠብ ያለ ውጤት የለም፤

10) በሠራዊቱ ተስፋ የቆረጠው አገዛዙ ከኦሮሞ ክልል  አዲስ ተዋጊ በገፍ ጭኖ ወደአማራ ጠቅላይ ግዛቶች እያዘመተ ነው፤ ይህ የአንድ ፓርቲና ግለሰብ ወንበር ጠባቂ የሆነ ወራሪ ሰራዊት ዕጣ ፈንታው ምርኮ፣ መቁሰልና አፈር መግባት ከመሆን አይዘልም!!! 

በአማራ ክልል አይቀሬ ሽንፈት እንደሚጠብቀው እየደረሰበት ካለው ከባድ ኪሳራ የተረዳው አገዛዙ፣ በእነ ሺመልስ አብዲሳ በኩል በኦሮሞ ክልል ምስኪን አርሶአደር እየሰበሰቡ በማሰልጠን “ሥልጣን ጠብቁ” በሚል ለለየለት የዘር ማጥፋት እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የአማራ ሕዝብ የገባበት የህልውና ጦርነት ተገዶ ስለመሆኑ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህ ጦርነት ለአማራ ሕዝብ የህልውና ጦርነት ነው፤ ጠላቶቹ ሊያጠፉት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ እርሱም እንደሕዝብ ተነስቶ ጠላቶቹን በመመከት ላይ ነው…! አማራ ጠሎቹ፦ የዓድዋ ድል ቁስለኞች፤ የፋሽስት ዓላማ ወራሾች፤ ኢትዮጵያን ‹‹መከላከያ›› የሌላት ሀገር ቢያደርጓትም፤ በአይቀሬው የአማራ ሕዝብ ድል ማግሰት ኢትዮጵያ የዓድዋ ድል ታሪክ ወራሽ፤መላ ልጆቿን የሚመስል ብሔራዊ ጦር ትገነባለች!!

ኢትዮ 251 ሚዲያ!