የዘንድሮው የአፍሪካ ምርጡ የባንክ ባለሙያ- አቶ አድማሱ ታደሰ
ሞሪሺየስ መቀመጫውን ያደረገው የንግድ እና ልማት ባንክ (Trade and Development Bank- TDA) ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አድማሱ ታደሰ ‘Banker of the Year’ ወይም ‘የአፍሪካ ምርጡ የባንክ ባለሙያ’ በመባል በትናንትናው እለት በናይሮቢ፣ ኬንያ በተደረገ ትልቅ ፕሮግራም ላይ ሽልማት ተቀብለዋል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ በዋና አዘጋጅነት በተሳተፈበት በዚህ ፕሮግራም ላይ አቶ አድማሱ ከሰባት ሌሎች እጩዎች መሀል በአንደኝነት በመመረጥ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።
የባንክ ባለሙያው ከዚህ ቀደም በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በአለም አቀፍ ፋይናንስ አማካሪነት፣ በኮርፖሬት እቅድ አስተባባሪነት፣ እንዲሁም ኒውዮርክ በሚገኙ ድርጅቶች ውስጥ በፋይናንስ ተንታኝ ባለሙያነት ሰርተዋል።
በአሁን ወቅት የሚመሩት TDA ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የበርካታ ቢልዮን ዶላሮች ፕሮጀክቶችን ያንቀሳቅሳል።
(ለትርፍ የሚሰሩ የጋና፣ ናይጄርያ… ወዘተ መፅሄቶች እና ጋዜጦች የሀገራችን የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን ሸለሙ ብለው በዜና የሚያጨናንቁን የመንግስት ሚድያዎች ይህን በአፍሪካ ልማት ባንክ አዘጋጅነት በተካሄደ፣ በርካታ የኢትዮጵያ የባንክ ሀላፊዎች ጭምር የተገኙበትን እና አንድ ኢትዮጵያዊ ‘ምርጥ የባንክ ባለሙያ’ የብሎ የተሸለመበትን ፕሮግራም አልፈውታል) Via Elias Meseret