በኬንያው ዊሊያም ሩቶ ጉብኝት እና በዋይት ሃውስ አቀባበል የተበሳጨው አብይ አሕመድ አሜሪካን አገር የሚገኙና ለዋይት ሃውስ እና ለስቴት ዲፓርትመንቱ ቅርብ የሆኑ ሎቢስቶች በጠየቁት ገንዘብ ተቀጥረው የዋይት ሃውስ ጉዞ እንዲያመቻቹለት ማዘዙ ከተቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ወደ አሜሪካ ተኩዘው ይፋዊ የሆነ የክብር አቀባበል ከዋይት ሃውስ የተደረገላቸው ሲሆን የአለም ሚዲያዎችም ይህንን በስፋት ዘግበውታል። የአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ባወታው አተር ያለ መግለቻም የዊሊያም ሩቶን አቀባበል ከንጉሰ ነገስት ሃይለ ስላሴ አቀባበል ጋር በማመሳካር የዊሊያ ሩቶን የአሜሪካ ጉዞ እጅግ ልዩና ከንጉሰ ነገስቱ በስተቀር ለአፍሪካውያን መሪዎች ተደርጎ የማያውቅ መሆኑን ገልጾ ፅፏል።
የአለም ሚዲያዎች ዘገባ እና የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ያበሳጫቸው አብይ አሕመድ በቢሯቸው እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመቀናጀት ሎቢስዎች በጠየቁት ገንዘብ ተቀትረው የዋይት ሃውስ ጉዞ እንዲያመቻችላቸው ማዘዛቸው የተገለጸ ሲሆን በድርጅትም ይሁን በግለሰብ ደረጃ ለዋይት ሃውስ እና ለስቴት ዲፓርትመት ቅርብ የሆኑና ሊያሳኩ የሚችሉ ሎቢስቶች በአስቸኳይ እንዲቀጠሩ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፈዋል። ይህ ቅናት እና ብስጭት የወለደው የአብይ ዋይት ሃውስን በሩቶ ደረጃ የመጎብኘት አላማ ይሳካ አይሳካ ወደፊት የምናየው ይሆናል።
አብይ አሕመድ ችግኝ ተከልኩ በማለት የውሸት ቁጥር እና የውሸት ስራ በመስራት አለምን ለማታለል ቢሞክሩም የክላይሜት ቼንጅ ጋር በተያያዘ የኬኛው ሩቶ መሸለማቸው ሲታወስ አብይ አሕመድ በዚህ ሽልማት የተሰማቸው ብሽቀት ለማካካስ ሙሳ ፋኪንና በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑን ደሚቱን ሚሊዮን ዶላሮችን አስታቅፈው ወደ አንድ የሽልማት ድርጅት በመላክ ሽልማት መግዛታቸው ይታወሳል።