
ከ 4 ሰአት በፊት
ቻይና ሰው አልባ መንኮራኩሯ በተሳካ ሁኔታ ማንም ሞክሮ በማያውቀው የጨረቃ ክፍል ማረፍ መቻሉን ገለጸች።
ቻንግ 6 የተበለው መንኮራኩር እሑድ ጥዋት በደቡብ ዋልታ-አይትከን ማረፉን የቻይና ብሔራዊ የጠፈር አስተዳደር (ሲኤንኤ) አስታውቋል።
የዛሬ ወር ገደማ ጉዞ የጀመረው መንኮራኩር ዓለማው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ውድ ድንጋይ እና አፈርን ለመሰብሰብ ያለመ ነው ተብሏል።
በዚህም በደቡብ ዋልታ ላይ ካለው ግዙፍ ጉድጓድ ውስጥ የተወሰኑትን የጨረቃን ጥንታዊ አለቶች ማውጣት ይችላል።
የግንኙነት መስመር መቆራረጥ ያለበት ቦታ በመሆኑ መንኮራኩሩ ከመሬት በተቃራኒ በሚገኘው የጨረቃ ክፍል ስለማረፉ ለማረጋገጥ ስጋቶች ነበሩ። ቻይና በ2019 ቻንጊ-4 መንኮራኩርን በማሳረፍ ይህንን ስኬት ያስመዘገበችም ብቸኛዋ አገር ነች።
ከዌንቻንግ የጠፈር ማስወንጨፊያ ማዕከል ወደ ህዋ ከተመነጠቀ በኋላ፣ ቻንግ 6 ጨረቃን እየዞረ ለማረፍ ሲጠባበቅ ነበር።
በኋላም ከምድር ርቆ በሚገኘው የጨረቃን ክፍል ለማረፍ ችሏል።
መንኮራኮሩ ምቹ የሆነ ቦታ ለማረፍ በሚያደርገው ጥረት መሰናክሎችን በመለየት መንቀሳቀስ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ እና እንደጨለማው ሁኔታ የሚቀያየር ብርሃን የተገጠመለት መሆኑን ሲኤንኤን ጠቅሶ ዢኑዋን ዘግቧል።
- በታሪካዊው የደቡብ አፍሪካ ምርጫ ኤኤንሲ አብላጫ ድምጽ ለምን አጣ? የትኞቹስ ፓርቲዎች ከፍ አሉ?ከ 6 ሰአት በፊት
- የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን እናፈርሳለን ሲሉ ዛቱከ 5 ሰአት በፊት
- ሪያል ማድሪድ ዌምብሌይ ላይ ዶርትሙንድን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳከ 5 ሰአት በፊት
የቻይና መንግሥት መገናኛ ብዙሃን የተሳካው የመንኮራኩሩ ማረፍ “ታሪካዊ” ሲሉ ገልጸውታል።
መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ሲያርፍ በቤጂንግ ኤሮስፔስ የበረራ መቆጣጠሪያ ማዕከል “ከፍተኛ ጭብጨባ ነበር” ብሏል የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን።
መንኮራኩሩ ከማረፉ በፊት “በርካታ የምህንድስና ፈጠራዎች፣ ከፍተኛ የአደጋ ስጋት እና ከፍተኛ ችግር” ቅኝቶች ማድረግን እንደሚያካትቱ ገልጿል።
በማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ የጨረቃ ጂኦሎጂ ስፔሻሊስት የሆኑት ፕሮፌሰር ጆን ፔርኔት-ፊሸር “እነዚህን ማንም ሰው አይቶ የማያውቃቸው ድንጋዮች ልናይ የምንችልበት አጋጣሚ በመኖሩ ሁሉም ሰው በጣም ተደስቷል” ብለዋል።
በአሜሪካዋ አፖሎ እና በቀድሞ የቻይና ተልእኮዎች ላይ የተሰበሰቡተን ሌሎች የጨረቃ አለቶች ለማጥናት ዕድል አግኝተዋል።

የአሁኑ ከዚህ በፊት ድንጋይ ካልተሰበሰበት የጨረቃ ክፍል የሚገኝ በመሆኑ ፕላኔቶች እንዴት እንደተፈጠሩ የሚመልሱ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ሊመልሰዉ ይችላሉ ብለዋል።
እስካሁን የተሰበሰቡት አብዛኛዎቹ ድንጋዮች ከአይስላንድ ወይም ከሃዋይ ከሚገኙት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው እሳተ ገሞራዎች ድንጋዮች ናቸው።
በጨረቃ ሩቅ አቅጣጫ በኩል ያለው ድንጋይ የተለየ አፈጣጠር ሊኖረው ይችላል።
“ፕላኔቶች እንዴት ተፈጠሩ የሚሉ ዓይነት ትልልቅ ጥያቄዎችን እንድንመልስ ይረዳናል” ይላሉ ፕሮፌሰሩ።
በአሁኑ ተልዕኮው ወደ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ቁሳቁስ ለመሰብሰብ ያለመ ነው ሲል ሲኤንኤስኤ ገልጿል።