በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አልብስ አደፍራሽ እንደተገደሉ የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል።
የወረዳው አስተዳደር ኮምንኬሽን ቢሮ በወረዳ አስተዳዳሪው ላይ ከትናንት ወዲያ ግድያውን የፈጸሙት፣ “ጽንፈኛ” ሲል የጠራቸው ኃይሎች እንደኾኑ ገልጧል።
የወረዳው አስተዳደር፣ “ጽንፈኛ” ያላቸው ኃይሎች ግድያውን የፈጸሙት በምሽት ተሹልክልከው በመግባት ነው ብሏል።
ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር፣ ኹለት የሸዋሮቢት ከተማ ጸጥታ ኃላፊዎች በተመሳሳይ ኹኔታ እንደተገደሉ አይዘነጋም።