June 6, 2024 – Konjit Sitotaw 

የመጋቢ ቢኒያም ሽታዬ እና ነቢይ ኢዮብ ጭሮ ጨምሮ የ4 ግለሰቦች ፈቃድ ተሰረዘ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ዙሪያ የ3ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔን አሳውቋል።

የካውንስሉን ምክር ተቀበለው፤ ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው፤ ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት እንዲሰረዝ ተወስኗል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ፋስት መረጃ ተመልክቷል::

ሰርተፍኬታቸው የተሰረዘባቸው

1ኛ ነቢይ ኢዮብ ጭሮ

(ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ)

2ኛ መጋቢ ካሳ ኪራጋ

(ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን)

3ኛ መጋቢ መዝገቡ ሚስጥሩ

(የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን)

4ኛ መጋቢ ቢኒያም ሽታዬ

(የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ)