
ከ 5 ሰአት በፊት
የዴንማርኳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን በመዲናዋ ኮፐንሃገን ጎዳና ላይ በአንድ ግለሰብ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ቢሯቸው አስታወቀ።
ከጥቃቱ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሯ “በከፍተኛ ሁኔታ መደናገጣቸውን”ም እንዲሁ ቢሯቸው አክሏል።
ጥቃቱ የተፈጸመው በከተማዋ ማዕከል በሚገኝ አደባባይ ላይ ሲሆን አንድ ግለሰብ ወደ እሳቸው በማምራት መትቷቸዋል።
የመታቸው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የአውሮፓ ኮሚሽን ኃላፊ ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን “በአውሮፓ ከምናምንበት እና ከምንታገለው ሁሉ የሚጻረር አጸያፊ ተግባር ነው” ሲሉ ጠርተውታል።
“ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሪድሪክሰን አርብ አመሻሽ ላይ በኮፐንሃን፣ ኩልቶርቬት በአንድ ግለሰብ ተመትተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሯ በድርጊቱ ተደናግጠዋል” ይላል ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ።
- ተመድ የእስራኤልን ጦር በህጻናት ላይ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ዝርዝር ውስጥ አካተተከ 6 ሰአት በፊት
- አዲሱ የጥምር መንግሥት በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?ከ 7 ሰአት በፊት
- የኢትዮጵያ ሠራዊት ከሶማሊያ መውጣት ለአልሻባብ የመጠናከር ዕድል ይፈጥራል?7 ሰኔ 2024
ፖሊስ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና ጉዳዪን እያጣራ መሆኑን ቢገልጽም ተጨማሪ ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥቧል።
ግለሰቡ ጠቅላይ ሚኒስትሯን ለምን እንደመታቸው የተባለ ነገር የለም።
ማሪ አድሪያን እና አና ራቭን የተባሉ ሁለት የዓይን እማኞች “አንድ ግለሰብ ከተቃራኒ አቅጣጫ መጥቶ ሄዶ ትከሻቸውን በከባዱ ጎሸማቸው። ይህም እንዲንገዳገዱ አድርጓቸዋል።” በማለት ለሃገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን የጎሸማቸው በከባዱ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሯ መሬት ላይ አልወደቁም ብለዋል።
በመቀጠልም ወደ አንድ ካፌ አምርተው መቀመጣቸውን እኚሁ የዓይን እማኝ አስረድተዋል።
ጥቃቱ የደረሰው ዴንማርክ በአውሮፓ ህብረት ምርጫ ላይ ድምጽ ከመስጠቷ ከሁለት ቀናት በፊት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዴንማርክ ጥምር መንግስት ውስጥ ትልቁ ፓርቲ እና የግራ ዘመም ፖለቲካን የሚያራምደው የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ መሪ ናቸው።
የ46 ዓመቷ ሜት ፍሪድሪክሰን ወደ ስልጣን የመጡት በአውሮፓውያኑ 2019 ሲሆን ይህም በዴንማርክ ታሪክ ትንሿ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓቸዋል።