June 8, 2024 

“ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች ለኢትዮጵያ” መንግሥት በጋዜጠኞች፣ በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ በኾኑ ሰዎች እና ፖለቲከኞች ላይ የሚፈጽመው “የዘፈቀደ እስር” እንዳሳሰበው ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ድርጅቱ፣ የመንግሥት ርምጃዎች የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የማፈን አዝማሚያን ያመለክታሉ ብሏል።

መንግሥት “በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚፈጽማቸውን ጥሰቶች” እንዲያቆም እና የዜጎችን የመናገርና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲያከብር ድርጅቱ ጥሪ አድርጓል።

ድርጅቱ፣ መንግሥት ሀሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው ያሠራቸውን ግለሰቦች ባስቸኳይ እንዲፈታም ጠይቋል።