
ከ 4 ሰአት በፊት
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ተቀናቃኛቸው በአውሮፓ ኅብረት አገራት የፓርላማ ምርጫ ላይ ስኬት ማግኘታቸውን ተከትሎ የፈረንሳይ ፓርላማን በትነው በቅርቡ አስቸኳይ ምርጫ እንደሚደረግ ገለጹ።
ማክሮን ባልተጠበቀ ውሳኔያቸው የአገሪቱ ፓርላማ ተበትኖ ሰኔ 23 እና 30/2016 ዓ.ም. አስቸኳይ ምርጫ እንደሚደረግ ከቤተ-መንግሥታቸው በቀጥታ በተላለፈ የቴሌቪዥን ስርጭት ተናግረዋል።
በፈረንሳይ ፖለቲካ ውስጥ የማክሮን ተቀናቃኝ የሆኑት የማሪን ለ ፔን ቀኝ ዘመም ናሽል ራሊ ፓርቲ በአውሮፓ የፓርላማ ምርጫ ስኬትን አስመዝግቧል።
ሁለተኛ ዙር የስልጣን ዘመናቸውን ከጀመሩ ሁለት ዓመታት እንኳ ያልሆናቸው ማክሮን፤ “የፓርላማውን የወደፊት እጣን በተመለከት በድምጻችሁ ውሳኔ እንድትሰጡ ዕድሉን ለእናንተ እሰጣለሁ” ብለዋል።
- ሩሲያ ታላላቅ ሳይንቲስቶቿን እያሰረች በአገር ክህደት የምትከሰው ለምንድን ነው?ከ 5 ሰአት በፊት
- ቻይናውያን ሴቶች ማኅበራዊ ሚዲያን ገንዘብ ለመቆጠብ እየተጠቀሙበት ነውከ 5 ሰአት በፊት
- የቀደምት አፍሪካውያን ቋንቋ ነው የሚባለው እና ሊጠፋ የተቃረበው ኢትዮጵያዊው ቋንቋ – ጫቡ9 ሰኔ 2024
በዚህ የአውሮፓ የፓርላማ ምርጫ በኅብረቱ አባል አገራት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች ብዙ ወንበር እያገኙ ነው። የኦስትሪያው ፍሪደም ፓርቲ እንዲሁም የፈረንሳዩ ናሽናል ፓርቲ ያልተጠበቀ ስኬትን ተጎናጽፈዋል።
በጀርመን፣ ግሪክ፣ ፖላንድ፣ ስፔን እንዲሁም በሃንጋሪ ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች ብዙ ድምጽ አግኝተዋል።
ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች 32 በመቶ የአውሮፓ ፓርላማን እንደሚይዙ ተገምቷል።
በፈረንሳይ የማክሮን ሬነሳንስ ፓርቲ ከተቀናቃኙ ናሽል ራሊ ፓርቲ በእጥፍ ያነሰ ድምጽ ነው ማግኘት የቻለው።
የአውሮፓ ምርጫ ምንድን ነው?
በየአምስት ዓመቱ 27 የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ዜጎች የኅብረቱን የፓርላማ አባላት ምርጫን ያደርጋሉ።
መቀመጫቸውን ቤልጂየም ብራሰልስ ያደረጉት የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባላት የአባል አገራት ዜጎችን ፍላጎት በአውሮፓ ደረጃ ያስጠብቃሉ።
የፓርላማ አባላቱ ከአባል አገራት መንግሥታት ጋር በመጣምር የአባል አገራቱን ምጣኔ ሃብት፣ ደኅንነት እና የአየር ንብረት ለውጥን የተለመከቱ ሕጎችን ያረቃሉ።
ፓርላማው የአውሮፓ ኅብረት በጀትን ያጸድቃል፣ የገንዘብ ወጪን ይቆጣጠራል። የኅብረቱን ኮሚሽንም ይሾማል እንዲሁም ይቆጣጠራል።
በኅብረቱ ያሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ ተሳታፊ የሚሆኑ ዕጩዎቻቸውን ያቀርባሉ። ፓርላማው 705 ወንበሮች ያሉት፤ ትልቅ አገር ለፓርላማው በርካታ አባላትን ያወጣል በሚለው መርህ ጀርመን 96፣ ፈረንሳይ፣ 81 እንዲሁም ጣሊያን 76 ወንበሮችን በመያዝ ቀዳሚ ናቸው። እንደ ላክሰመበርግ እና ማልታ ያሉ አገራት ደግሞ 6 አባላትን ወደ ፓርላማው ይልካሉ።