የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም
የምስሉ መግለጫ,የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም

ከ 5 ሰአት በፊት

በየትኛውም ጊዜ ዓለምን የሚያሰጋ የጤና ቀውስ ሲፈጠር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አገራት፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎችም የዓለም ጤና ድርጅትን መመሪያ እና ድጋፍ ይጠብቃሉ።

ድርጅቱ ተልዕኮዬ የተሻለ የጤና ሁኔታን ማቅረብ እና “ለሁሉም በየቦታው በእኩልነት ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ ሕይወት እንዲኖር” ማገዝ ነው ይላል።

ይህ በስዊትዘርላንድ መቀመጫውን ያደረገው ዓለም አቀፍ ተቋም ከ79 ዓመት በፊት በ1940 (እአአ) ነበር የተመሠረተው።

የዓለም ጤና ድርጀት የመንግሥታቱ ደርጅት አንደኛው አካል ሲሆን፤ ዓላማው ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሰዎችን ጤንነት እና ደኅንንት መከታተል ነው።

ያም ብቻ ሳይሆን በሽታዎች የሚወገዱበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነትም አለበት።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት

ድርጅቱ 194 አባል አገራት አሉት። ይህንኑ ተቋም ለ10 ዓመታት በበላይነት የመሩት የወቅቱ ዳይሬክተር የትውልደ አገር ኢትዮጵያም ከአባል አገራቱ መካከል አንዷ ናት።

ይህ ድርጅት የክትባት ዘመቻ፣ በአደጋ ጊዜ ሰዎችን የመርዳት እና አገራትን በጤናው ዘርፍ መደገፍን ጨምሮ በርካታ ፕሮጅክቶች ላይ ይሠራል።

በተጨማሪም የምግብን ደኅንነት፣ የመድኃኒቶችን የሙከራ ሂደት፣ የበሽታዎችን የህክምና ሂዳት ደረጃን (standardisation) ጨምሮ ልዩ ልዩ መመሪያዎችን ማዘጋጀትም ተግባሩ እንደሆነ ደርጅቱ ይገልጻል።

የድርጅቱ አባል አገራት እና የእርዳታ ተቋማት የገንዘብ ምንጩ ናቸው። ባለፈው ዓመት ለጠቅላላ ተግባሩ 6.72 ቢሊዮን ዶላር በጀት መድቦ ነበር።

የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ እና የጤና ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ ድርጅቱን እየመሩ ነው።

እሳቸው የሚመሩት ድርጅት የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ሰብአዊ ቀውሶች እና ወረርሽኞች ሲከሰቱም ከዓለም መንግሥታት ጋር በጋራ ይሠራል።

እንደ ጋዛ ባሉ የጦርነት ቀጠናዎች ውስጥም ችግር ላይ ለወደቁ ሰዎችም የጤና እርዳታን ያቀርባል።

በሌላ በኩል በታዳጊ አገራት የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚሠራ ሲሆን፣ ይህንን የሚያደርገው ለጤና ባለሙያዎች በአገራቸው ውስጥ ሥልጠና በመስጠት ነው።

ይህም ብቻ አይደለም፣ መረጃ የሚሰጡ እና ለፖሊሲዎች ግብዓት ሊሆን የሚችል መረጃ እና የእውነታ ማሳያዎችን (factsheets) ያዘጋጃል።

የፈንጣጣ በሽታ ከጠፋ 30 ዓመታት መቆጠሩን በማስመልከት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የቆመ ሀውልት
የምስሉ መግለጫ,የፈንጣጣ በሽታ ከጠፋ 30 ዓመታት መቆጠሩን በማስመልከት በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት የቆመ ሀውልት

የክትባት መርሃ-ግብሮች

የዓለም ጤና ድርጅት ተላላፊ እና ተላላፊ የልሆኑ በሽታዎች ክትትል፣ መከላከል፣ ምርመራ፣ አንክንካቤ እንዲሁም ህክምና ትኩረቱ መካከል ሲሆኑ የአእምሮ ጤና ጉዳይም እዚህ ውስጥ ይካተታል።

ከዚህም አልፎ ዓለም አቀፍ ዘመቻዎችን በመጀመር እና በማስተባበር በሽታዎችን የማጥፋት ተግባርም ይከውናል።

ለምሳሌ በ1966 (እአአ) ይፋ ያደረገው የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም የማዳበር መርሃ-ግብርም ተጠቃሽ ነው።

መርሃ-ግብሩ ሲጀመር በዓለም ዙሪያ ህጻናትን ማዕከል በማድረግ ለስድስት በሽታዎች ሲሰጥ ቆይቷል። ተቅማጥ፣ ከፍተኛ ሳል፣ ቲታነስ፣ ፖሊዮ፣ ኩፍኝ እና ሳምባ በክትባቱ የተጠቃለሉ በሽታዎች ናቸው።

ይህ መርሃ-ግብር በኋላ ላይ 30 ተጨማሪ ክትባቶችን አካትቷል። ከእነዚህ ውስጥ 13ቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ ሲሆን፣ የተቀሩት 17ቱ ደግሞ በተለየ አካሄድ ለተወሰኑ ቦታዎች ብቻ የሚቀርብ ነው።

ፖሊዮ ከፓኪስታን እና አፍጋኒስታን በስተቀር ከሁሉም አገራት ጠፍቷል
የምስሉ መግለጫ,ፖሊዮ ከፓኪስታን እና አፍጋኒስታን በስተቀር ከሁሉም አገራት ጠፍቷል

የዓለም ጤና ድርጅት ስኬቶች ምንድን ናቸው?

በዓለም አቀፍ ደረጃ የፈንጣጣ በሽታ ትርጉም ባለው ደረጃ እንደቀነሰ ይነገራል። ይህም የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጀት ትልቁ ስኬት ነው።

ፈንጣጣ ለሚሊዮኖች ጉዳት እና ሞት ምክንያት የነበረ በሽታ ነው።

እናም የዓለም ጤና ድርጅት ፈንጣጣን ለመከላከል በ1959 ይፋ ያደረገው ዘመቻ ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል። በዚህ ዘመቻ ለበርካታ ዓመታት በዓለም ዙሪያ በሽታውን በመከታተል እና በመከላከል በኩል በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል።

ድርጅቱ ከአስርት ዓመታት በላይ የቆየበት ሥራው ውጤት እንዳመጣ እና ፈንጣጣ ለዓለም ሕዝብ ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ በዚህ መጠን ሥርጭቱን የቀነሰው የኢንፌክሽን በሽታ የለም። ይህ ውጤት “በሕብረተሰብ ጤና ታሪክ ጎልቶ የሚታይ እና ከፍተኛ ስኬት የተገኘበት” ነው ሲል ድርጅቱ ይገልጸዋል።

ሌላኛው ፖሊዮ ነው።

በዓለም ጤና ድርጀት አስተባባሪነት በተደረገ ጥረት ከፓኪስታን እና ከአፍጋኒስታን በስተቀር በሁሉም አገራት ፖሊዮ ጠፍቷል። በዚህም ድርጅቱ ይመሰገናል።

ከዚህ በተቃራኒ፣ በ1955 ይፋ ሆኖ በ1961 ያበቃው ወባን የማጥፋት መርሃ ግብር ያመጣው ውጤት ዝግ ያለ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ወሳኝ አካል የሆነው እና ከሁሉም አባል አገራት ተወካይ ያለው፤ እንዲሁም በየዓመቱ ለምክክር የሚቀመጠው ጠቅላላ ጉባኤ ከ1955 አንስቶ እስከ 2007 ድረስ በየጊዜው ወባን በማጥፋት በኩል ያለውን ዓላማ ለማሳካት ቃሉን ሲያድስ ቆይቷል።

በአውሮፓውያኑ 2007 አስራ ሁለት አገራት ከወባ ሥርጭት ነጻ መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። የዓለም ጤና ድርጅት ያዘጋጀው “ዓለም አቀፍ ስትራቴጂ” በቀጣዩ ስድስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ በ30 አገራት ወባ ይወገዳል የሚል ነው።

በ2013 ድርጅቱ የመጀመሪያውን የወባ መከላከያ ክትባት ለህጻናት እንዲውል ምክ ረሀሳብ አቅርቧል። ከሁለት ዓመት በኋላ ማለትም ባለፈው ዓመት ደግሞ የወባ ክትባት ዘመቻን አስጀምሯል።

ይህ መርሃ ግብር፣ የመጀመሪያውን የወባ ክትባት ለ12 የአፍሪካ አገራት 18 ሚሊዮን ጠብታ (dose) በቀጣዩ ዓመት ለማደረስ አቅዷል።

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ነበረበት
የምስሉ መግለጫ,የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ነበረበት

የዓለም ጤና ድርጅት በምን ይተቻል?

የዓለም ጤና ድርጀት ከአስር ዓመት በፊት በምዕራብ አፍሪካ አገራት ለኢቦላ ወረርሽኝ የሰጠው ትኩረት ‘እዚህ ግባ’ የሚባል አይደለም በሚል ክፉኛ ተተችቷል። ድርጅቱ በቂ መረጃ ባለመስጠት እና ያሰማራቸው ባለሙያዎች ብቁ አይደለም በሚል ተወቅሷል።

የድርጅቱ ተቆርቋሪዎች ግን ከዚህ የተለየ ሀሳብ ሲያራምዱ ተደምጠዋል። ድርጅቱ ላይ በወቅቱ የቀረበው ትችት ያልተገባ እና ሰዎች ሲጠብቁት የነበረው ምላሽ ከእውነታው የራቀ ነው ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጀት የበሽታዎችን መረጃ እና ትንተና ሊያቀርብ ቢችለም፣ በቀጥታ እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን ግን የለውም። ይህንን ማድረግ የሚችለው አባል የሆኑ አገራት እርዳታ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ብቻ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሰጠው ምላሽም ከዓለም ዙሪያ ልዩ ልዩ ትችቶች ቀርበውበታል።

በ2012 ዓ.ም የያኔው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ድርጅቱን ለቃ እንደምትወጣ ዝተው ነበር።

ምክንያት ያሉት ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት ያደረገው ጥረት አንስተኛ ነው በሚል ነው። በተጨማሪም ድርጅቱ በቻይና ቁጥጥር ስር ወድቋል የሚል ክስም አሰምተዋል።

አሜሪካ የድርጅቱ ትልቁ ገንዘብ ረጂ በመሆኗ ያ ዜና በተቋሙ ላይ ከፍተኛ መረበሽን የፈጠረ ነበር።

በተከታዩ ዓመት ትራምፕ ከሥልጣናቸው ወረደው ጆ ባይደን ሲተኩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዓለም ጤና ድርጅት ላይ የነበራቸውን ዕቅድ ቀልብሰውታል። አገራቸው ለድርጅቱ የምታደርገውን የገንዘብ እና ፖለቲካዊ ድጋፍም እንደምትቀጥልብት አረጋግጠዋል።

ድርጅቱ ያዋቀረው የባለሙያዎች ቡድን የኮቪድ 19ን ወረርሽኝ ቀደም ብሎ መከላከል የሚቻል እንደነበር ድምዳሜ ሰጥቶ ነበር። ቀጥሎም በድርጅቱ እና በአገራት መካከል የነበረው ትብብር በቂ እንዳልነበረ እና ወረርሽኙ እንዲከፋ ምክንያት ሆኗል ብሏል።

ቡድኑ የዓለም ጤና ድርጅት የአደጋ ጊዜ ኮሚቴ፣ በቻይና የተቀሰቀሰውን በሽታ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ብሎ ለማወጅ ዘግይቷል ሲልም ምርመራው ደምድሟል። እንደ ባለሙያዎች ቡድኑ ከሆነ ኮቪዲ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መባል የነበረበት ከታወጀበት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ነበር።

ቡድኑ የኮሮናቫይረስ ሥርጭት ቀጣዩን ወረርሽኝ ለመከላክል የተሻለ ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና የዓለም ጤና ድርጅት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሚያስፈልገው ጠቋሚ ነውም ብሏል።