July 14, 2024 

በትግራይ የታጠቁ ኃይሎችና የውጭ ዜጎች ከሚሳተፉበት የወርቅ ሕገወጥ ቁፋሮና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ከሚያዝያ ወዲህ ብቻ ከ20 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ በምርመራ ማረጋገጡን ሪፖርተር ዘግቧል።

በተለይ እንዳባጉና ወረዳ የሚገኘው የትግራይ ጀኔራሎች የሚቆጣጠሩት “ራህዋ” የወርቅ ማውጫ ከፍተኛ ሕገወጥ የወርቅ ቁፋሮና ኮንትሮባንድ እንደሚካሄድበትና ተዋናዮቹ የቀድሞ የሕወሃት ተዋጊዎች፣ ወጣቶች፣ ስደተኞችና ቻይናዊያን እንደኾኑ ዘገባው ጠቅሷል።

ዘገባው፣ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በ”ሒንጻት” የወርቅ ማውጫ ከኹለት ወራት በፊት በቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎችና በጥበቃዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 22 ሰዎች እንደሞቱ መስማቱን ገልጧል።

ሕገወጡ ወርቅ ወደ አዲስ አበባ፣ አሥመራ፣ ሐርጌሳ፣ ናይሮቢ እና ካምፓላ እንደሚሸጥና ከዚያም መዳረሻው ዱባይ እንደኾነ ምንጮች ስለመናገራቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።