July 14, 2024 – Konjit Sitotaw 

ከትናንት በስቲያ ከጅማ እስከ ወለጋ እንዲሁም እስከ ወላይታ የተሰማው ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ ምንድን ነበር?

የከባድ ጦር መሳርያ ድምፅ ነው፣ መብረቅ ነው፣ ከሌላ አለም የመጣ ባዕድ ነገር ነው ወዘተ የሚሉ በርካታ መላምቶችን ተመልክቻለሁ።

በጠፈር ሳይንስ እና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት የአስትሮፊዚክስ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን በላይ ይህን መረጃ ሰጥተውኛል:

– ከተመለከትኳቸው ምስሎች መረዳት የቻልኩት ወደቁ የተባሉት አካላት የሚቲዮራይት ስብርባሪ መሆናቸውን ነው

– የጅማ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ዲፓርትመንትን በዚህ ዙርያ አነጋግሬ ያገኘሁት ምላሽ ተመሳሳይ ነው፣ ወድቆ የተገኘው አካል ወደ ዩኒቨርስቲው ለምርመራ እንዲወሰድ ሀሳብ አቅርቤያለሁ

– ይህ ከፍተኛ ድምፅ የተሰማው ከደቡብ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ነው፣ አጋሮ አካባቢ አንዳንድ ስብርባሪ ተገኝቷል

ሚቲዮራይት ከሌላ ጠፈር (outer space) በመነሳት ምድር ላይ የሚያርፍ ድንጋይ/አለት ሲሆን ወደ ምድር ከባቢ አየር ሲገባ በሰበቃ (friction)፣ ሀይለኛ ግፊት እና በኬሚካል ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ድምፅ እና ብርሀን ይፈጥራል።

Credit: ዶ/ር ሰለሞን በአሁኑ ወቅት የአለም አቀፈ አስትሮኖሚካል ህብረት ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አማካሪ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። ለሙያዊ አስተያየታቸው አመሰግናለሁ።

ሙሉ መረጃው ኢትዮጵያ ቼክ ላይ ይገኛል: https://t.me/ethiopiacheck/2379