Gidena Medhin is feeling curious.

  · 

የኢህአፓ ነገር ትዝ አለኝ …. በሀገራችን የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ኢህአፓ የተለመደ ነባር ስም ነው።

ሶስት ነገር ፦

1. ቆይቷል። አንዴ አአዩ ፕሬስ “Tower in the Sky” የተባለ የሂወት ተፈራ መፅሐፍ ልገዛ የሄድኩኝ ጊዜ የዚህ ተቋም ሰራተኛ ወ/ሮ መስታወት እንዲህ አሉኝ፡፡

👉🏾 የ18 ዓመት ልጄ በሁለት ቀናት “Tower in the Sky”ን አንብቦ ከጨረሰው በኋላ … “እማዬ ከዛሬ ጀምሮ ኢህአፓ ነኝ! ” ነኝ አለኝ።

2. ጥቂት የማይባሉ የኢህአፓ መስራቶች የእንደርታ ሰዎች ነበሩ። መስፍን ሃፍቱ (በአሜሪካ የኢህአፓ ቀደምት መስራች)፣ ቢንያም አዳነ፣ ዮሴፍ አዳነ፣ ፕሮፌሰር ዓለም ሃፍቱ፣ ዶ/ር ሃይሉ ሃፍቱ ወዘተ የሓረቖ (እንደርታ ) ተወላጆች ናቸው።

3. ብዙ የኢህአፓ መሪዎች (ብርሃነ መስቀል ረዳ፣ ዶ/ር ተስፋይ ደበሳይ፣ ዘሩ ክሕሽን፣ ፀሎተ ህዝቅያስ ፣ ጋይም ወዘተ) የትግራይ ልጆች እና እንዲሁም የኢህአሠ የመጀመሪያ የትግል ቦታው ዓሲምባ ( ዓጋመ፣ ትግራይ) የነበረ መሆኑና ከትግራይ ህዝብ ጋር ልዩ ትስስር ነበረው።

በእኔ እይታ፣

1. The Generation … በክፍሉ ታደሰ… ያ ትውልድ (በሚል ወደ አማርኛ ተተርጉሟል።) ፣

2.Tower in the Sky በሂወት ተፈራ፣ ማማ በሰማይ (በሚል ወደ አማርኛ ተተርጉሟል።)

3. የዓሲምባ ፍቅር፣ በካሕሳይ ኣብርሃ፣

4. ዳኛው ማነው ፣ በታደለች ኃይለ ሚካኤል

5. Yankee Go Home በአያሌው ይማም (ሙክታር) የተባሉትን መጽሐፍት ብታነቡ የ1970ዎቹ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ለመረዳት ይረዳቹኋል።

ደስ የሚለው፣

ሁሉም መፅሐፍት ውስጠ- ሚስጢሩን በሚያውቁ (from the horses mouths) በራሳቸው በባለታሪኮቹ (የኢህአፓ ታጋዮች) የተፃፉ መሆናቸው ነው። እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረቡት መፅሐፍት የቋንቋው ጥራቱ፣ ፍሰቱና የሀሳብ ንፅረቱ የአፍ መፍቻ ያህል ይፀዳል!

የተለያዩ ምንጭ ያላቸው መፅሐፍት እናንብብ!

እውነታውን እንረዳ !

አንሸወድ!