July 15, 2024 – Konjit Sitotaw 

በተከታታይ ቀናት አስራ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የጎንደር ቀጠና ውጊያ፤ በጠላት ላይ እሳት እየዘነበበት መሆኑ ይታወቃል። ጠላት ይህን ለመቀልበስ የውጊያ ዕቅድ ክለሳ አድርጓል።

በተለይም ጎንደር ከተማን ግማሽ ቀለበት ውስጥ ያስገባውን የፋኖን ኃይል ለመምታት ፋኖ በጠነከረባቸው ግንባሮች ከጀርባ በኩል ለመምታት የብልጽግና አገዛዝ የውጊያ ዕቅድ ክለሳ አድርጓል።

እንደወታደራዊ ምንጮቻችን መረጃ የመጀመሪያውን የውጊያ ዕቅድ ክለሳ የበለሳ ደጋማውን ክፍል (ደጎማ ከተማን) ይዞ => በደንቀዝ በኩል ከጀርባ በሰሜን-ምስራቅ አቅጣጫ ወደጎንደር ከተማ ዙሪያ በማጥበብ ፋኖን የቀለበት-ቀለበት ውጊያ ውስጥ በማስገባት ለማፈን አቅዷል።

ይህን ለማሳካት ሰሞኑን ከገባው በተጨማሪ ትላንትና ዛሬ አዳዲስ የኮማንዶ ኃይል በወታደራዊና ሲቪል አውሮፕላን ጭምር በተከታታይ ገብቷል።

በተጨማሪም የሰሜን ምዕራብ ዕዝ “የመከላከያ ልዩ ኃይል” የሚል ስያሜ ያለው ከመደበኛው ተዋጊ የተሻለ አቅም “አለው” ያሉትን ኃይል በሽፋን ሰጭነና ቆረጣ ማስገባት የተከለሰው የጠላት የውጊያ ዕቅድ አካል መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

በመሆኑም በጎንደር ቀጠና ባሉ ውጊያዎች የጠላት ኃይል ካለው አሁናዊ ስምሪት አኳያ (ኮማንዶው በመከላከያ ልዩ ኃይልና በጥምር ጦሩ ሽፋን ወደውጊያ እየገባ በመሆኑ) ፋኖ ፈጽሞ ጨበጣ ውጊያ እንዳያደርግ፤ ይልቁንም ፋኖ ባህላዊ ወጥመዶችን በስፋት እንዲጠቀም ይመከራል (ዝርዝሩን ጀግኖቹ የአማራ ልጆች ያውቁበታል)።

በአንዳንድ ወሳኝ የውጊያ ግንባሮች የጨበጣ ውጊያ የግድ ካስፍለገም ፋኖ በቁጥር ብልጫ ወስዶ ቢሆን ይመከራል። (ይህኛውንም ጉዳይ ጀግኖቹ ያውቁበታል)

ተጨማሪ ወሳኝ መረጃ
(የተደጋገመ ምክር አዘል መረጃ)

ማንኛውም ፋኖ በውጊያ ሰዓት ስልክ ይዞ ባይገባ፤ ከሬዲዬ መገናኛ ውጭ ከሻምበል መሪ በታች ስልክ ባይያዝ፤ በአጋጣሚ ስልክ ከያዙ ሁሉም Airplane mode ማድረግ ቢችሉ፤ የግድ ስልክ ይዘው የሚገቡ የፋኖ መሪዎች ደግሞ እንደ Bluetooth, hotspot wifi ያሉ የመረጃ መቀበያ መረቦች መጥፋታቸውን ማረጋገጥ የግድ ይላል።

በየትኛውም አውደ-ውጊያ፤ ወታደራዊ የስልጠና፣ ግምገማና የምክክር መድረኮች ላይ ስልክ እና ፋኖ ሁሌም መራራቅ እንዳለባቸው ይመከራል!!