July 17, 2024 

የጥላቻ ትርክት በማህበረሰብ ውስጥ መሰራጨቱ አለመተማመን አሳድጓል-አቶ ጌጥዬ ትርፌ

በኢትዮጲያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚታዩ የጥላቻ ትርክቶችና የደቦ ፍርዶች አለመተማመንን አሳድገው ማህበራዊ ትስስርንም በከፍተኛ ደረጃ እየበጣጠሱ ስለመሆኑ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፖለቲከኛው አቶ ጌጥዬ ትርፌ ገልፀዋል፡፡

በመንግስት ሹመኞችና በልሂቃን ዘንድ እንደ ፖለቲካ ትርፍ ማግኛ ተደርጎ የሚወሰደው የትርክትና የጥላቻ ጉዳይ ዋነኛ የሃገረ-መንግስት ችግር ሆኗል የሚሉት ፖለቲከኛው ይህን ለመፍታትም መንግስትም ሆነ በፖለቲካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተዋንያኖች ይህ ነው የሚባል ስራን ሲሰሩ አይታዩም ሲሉ ይተቻሉ፡፡

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ሁሉንም ማሳተፍ አለበት የሚባለው በምክንያት ነው ያሉት አቶ ጌጥዬ ሁሉም ህመምና ሁሉም በሽታ መድሃኒት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ጥያቄ ላለው አካልም ተገቢውን ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

መንግስት ዋነኛ የስልጣን አካል መሆኑን አውቆ ለሰላም ቁርጠኛ ሲሆን አለመታየቱ ችግሮችን አባብሷል በማለትም ቆም ብሎ ነገሮችን ሊመለከት ይገባል በማለትም ዋነኛው የቤት ስራ ያለው መንግስት ላይ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡