August 9, 2024 – Konjit Sitotaw
- “ አምስት የኢትዮጵያ ልዑካን በፖሊስ ታስረው ነበር “ አትሌት ገዛኸኝ አበራ
- “ ለሀላፊዎች ዘመድ እና ባለስልጣናት አበል መክፈል በዚች ደሀ ሀገር መቀለድ ነው “
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ገዛኸኝ አበራ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ፌዴሬሽኑን እንዲመረምር ጠይቋል።
ለኢትዮጵያ ከ56 ሰው ኮታ ብቻ መሰጠቱን የገለፀው አትሌት ገዛኸኝ አበራ “ እስከ ትላንት ፓሪስ እየገቡ ነው ይህ ሁሉ ሰው በህዝብ ገንዘብ ነው የሚመጣው “ ብሏል።
“ ከእያንዳንዳችን እናቶች መቀነት ተፈቶ በመጣ ገንዘብ ለሚጓዙ ለእነሱ ዘመዳ ዘመድ እና ባለስልጣናት 3000 ዶላር አበል መክፈል በዚህ ደሀ ሀገር ላይ መቀለድ ነው” ሲል አትሌት ገዛኸኝ አበራ ተናግሯል።
የይለፍ መግቢያ ባለማግኘቱ በሰው ግባ ተብሎ ገብቶ እንደነበር የገለፀው አትሌት ገዛኸኝ አበራ አሁን ግን እየከፈለ እየገባ እንደሚገኝ አትሌቱ ገልጿል።
“ መግቢያውን ሲቀባበሉ አምስት የኢትዮጵያ ልዑካን በፖሊስ ተይዘው ነበር “ ያለው አትሌት ገዛኸኝ አበራ ስማቸውን መጥቀስ ባልፈልግም ከሰጪውም ከተቀባዩም 48 ሰዓት ታስረዋል ብሏል።
“ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዝምድና የሚያፈሩበት ቤት ነው የሆነው ፖለቲከኞች የገቡበት ቤት ነው ሁሉም ወደ ሙያው ቢሄድ ይሻላል። “ አትሌት ገዛኸኝ አበራ
መረጃው ከሸገር ስፖርት የራድዮ ፕሮግራም የተወሰደ ነው።