
ከ 5 ሰአት በፊት
የአልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ኢማን ኸሊፍ እና የታይዋኗ ሊን ዩ-ቲንግ የሜዳሊያ ሥነ ሥርዓት ምሥሎች ከፓሪስ ኦሊምፒክ አይረሴ ዝርዝሮች ውስጥ እንደሚገቡ ይጠበቃል።
ባለፈው ዓመት በተካሄደው የሴቶች የዓለም ሻምፒዮና ውድድር መስፈርቶችን ባለማሟላታቸው ሁለቱም ከውድድሩ ውጪ ተደርገው ነበር። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሁለቱን ቦክሰኞች በፓሪስ የሴቶች ቦክስ ውድድር እንዲካፈሉ ማድረጉ የማያባራ ክርክር አስነስቷል።
ክርክሩ በጦፈበት በዚህ ወቅት ሳይንስ ደግሞ የተለያዩ የክሮሞሶም ውህዶችን እና ለስፖርት ምን ዓይነት ጥቅምን እንደሚሰጡ መረጃውን እንካችሁ እያለ ነው።
ጥናቱ ገና እንደቀጠለ ነው። ዕድሜያቸውን በዘርፉ ባሳልፉ ባለሙያዎች መካከል እንኳን የሳይንሱ ትርጓሜዎች የተለያየ ነው።
የፆታ ልዩነት ሂደት የሚጀምረው ፅንስ እያደገ ሲሄድ እንደሆነ እናውቃለን። አብዛኞቹ ሴቶች ሁለት X ክሮሞዞም (XX) አላቸው። አብዛኛዎቹ ወንዶች ደግሞ X እና Y ክሮሞዞም (XY) ያገኛሉ።
በእርግዝናው ወቅት ግን የአንዳንድ ህፃናት የመራቢያ አካላት እንደ አብዛኛው ሰው አይዳብርም።
ይህ ዲኤስዲ (የፆታ ዕድገት ልዩነት) በመባል ይታወቃል።
በማህፀን ውስጥ የሚፈጠሩ ጂኖች፣ ሆርሞኖች እና የመራቢያ አካላትን ጨምሮ 40 የሚያህሉ ሁኔታዎችን ያካተቱ ናቸው። ይህም የአንድን ሰው የፆታ ዕድገት ከሌሎች ሰዎች የተለየ ያደርገዋል ማለት ነው።
እነዚህ የክሮሞዞም ዕክሎች እምብዛም አያጋጥሙም። በኦሊምፒክ የቦክስ ውዝግብ ምክንያት ግን ክሮሞዞሞች ከፍተኛ ትኩረት ያገኛሉ።

በፆታ ጉዳይ መከራከሪያ ስለነበሩት ሁለቱ ቦክሰኞች ምን እናውቃለን?
የዓለም አቀፍ የቦክስ ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክሪስ ሮበርትስ ለቢቢሲ ስፖርት እንደተናገሩት ኤክስዋይ (XY) ክሮሞዞምች “በሁለቱም ቦክሰኞች” ውስጥ ተገኝተዋል።
ይህ ግን ያን ያህል ቀላል አይደለም።
እነዚህ የዘረመል ልዩነቶች በጣም ብዙ እና የተለያዩ ናቸው። አንዳንድ ባለሙያዎች ግን ዋይ (Y) ክሮሞዞም ያለው በሙሉ ወንድ እንዲሁም የY ክሮሞዞም የሌላቸው ሁሉ ሴት መሆናቸውን ማረጋገጥ አይቻልም ይላሉ።
በማንቸስተር ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ስፖርት ኢንስቲትዩት ባልደረባው ዶክተር አሉን ዊሊያምስ “የY ክሮሞዞም መኖርን በመመልከት ብቻ ወንድ ወይም ሴት ናት ለሚለው ጥያቄ መልስ አይሰጥም” ብለዋል።
“ብዙ የY ክሮሞዞም ያላቸው ሰዎች ወንድ መሆናቸው ጥሩ ጠቋሚ ነገር ነው… ግን ሁሌም ትክክለኛ አመልካች አይደለም።”
ለአንዳንድ ዲኤስዲ ላላቸው ሰዎች Y ክሮሞዞም ሙሉ በሙሉ ከወንዶች Y ክሮሞዞም ጋር ተመሳሳይ አይደለም። በተለያዩ ምክንያቶች ሊጎዳ ወይም ሊለዋወጥ ይችላል።
ወንድ ወይም ሴት መሆንን በተመለከተ ወሳኙ ነገር ኤስአርዋይ የሚባለው ልዩ ጂን ነው። ይህም ፆታን ወሳኝ የY ክሮሞዞም ይባላል።
የጄኔቲክ በሽታዎችን የሚያጠኑት የባዮሎጂ ምሁሯ ዶ/ር ኤማ ሒልተን “ይህ ወንድ ፈጣሪ ጂን ተብሎ የሚጠራው ነው” ብለዋል።
ኢማኔ ኸሊፍ እና ሊን ዩ-ቲን ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ መወዳደር እንደሌለባቸው የሚከራከር የፆታ ጉዳዮች በጎ አድራጎት ድርጅት አባልም ናቸው።
“የፆታ ዕድገት ዋና መቀየሪያ ነው” ይላሉ።
ዶ/ር ሒልተን ‘ወንድ-ፈጣሪ’ ብለው የሚጠሩትን ጂን ያጡ እና ከ XY ክሮሞዞም ጋር የተወለዱ አንዳንድ ሰዎች አሉ።
“እነዚህ ሰዎች ቴስቶስትሮን አያመርቱም። በጣም የተለመዱ የሴት የሰውነት አካላትን ያዳብራሉ” ሲል ዶ/ር ሒልተን ተናግረዋል።
ስለዚህ የXY ክሮሞዞሞችን የሚለየው ምርመራ የተሟላ ምሥል አይሰጥም። በኢማኔ ኸሊፍ እና ሊን ዩ-ቲን ጉዳይ፣ አይቢኤ የምርመራውን መንገድ በዝርዝር አልገለጸም።
ዶ/ር ሒልተን አክለውም XY ክሮሞዞም ባላቸው አብዛኞቹ ሰዎች ኤስአርዋይ “ወንድ-ፈጣሪ” ጂን እንዳለ ይናገራሉ።
“የጉርምስና ዕድሜ ላይ ሲደርሱ ቴስቶስትሮን ማመንጨት ይጀምራሉ። ይህም ወንዶች በስፖርት ውስጥ ያላቸውን ጥቅም የሚያረጋግጥ ነው” ብለዋል።
- በአልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ኢማኔ ኸሊፍ ላይ የተነሳው ውዝግብ ምክንያቱ ምንድን ነው?4 ነሐሴ 2024
- “በፆታዋ ምክንያት” በማኅበራዊ ሚድያ መነጋገሪያ የሆነችው ቦክሰኛ ኢማን ኼሊፍ ተጋጣሚዋን በ46 ሰከንድ አሸነፈች2 ነሐሴ 2024
- በሰኮንዶች ግጥሚያዋን ያቋረጠችው ጣሊያናዊቷ ቦክሰኛ አልጄሪያዊቷ ተፋላሚዋን ይቅርታ ጠየቀች2 ነሐሴ 2024

በጣም ታዋቂው ምሳሌ አቅርቡ ከተባለ ካስተር ሴሜንያ ትነሳለች። በ800 ሜትር የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ እና ሦስት ጊዜ ደግሞ የዓለም ሻምፒዮን ለመሆን በቅታለች።
ምንም እንኳን የዲኤስዲ አትሌቶች ከወንዶች ጋር ተመሳሳይ ጥቅም እንዳላቸው የሚያሳዩ ቀጥተኛ ማስረጃዎች የሉም ሲሉ ፕሮፌሰር አሉን ዊሊያምስ ተናግረዋል።
ዋናው የተፈጥሮ ሂደት ያለው ብልትን ለማሳደግ በሚያስፈልግው ጂን ውስጥ ነው። ይህም ወንዶች ብልታቸውን ለማሳደግ የሚያስፈልጋቸው ነው። ከካስተር ሴሜንያ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ያለው ማንኛውም ሰው በዚያ ጂን ውስጥ መባዛት ስለሚኖረው በተለምዶ መሥራቱን ያቆማል።
በማህፀን ውስጥ የወንድ ብልት የሚያድግበት የመጨረሻው ደረጃ እስኪደርስ ድረስ የወንድ የሰውነት አካልን ያዳብራ። ይህን ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ የሴት ብልትን ማዳበር ይጀምራሉ።
ነገር ግን የሴት የመራቢያ አካላትን አያዳብሩም። የማህፀን ጫፍ ወይም ማህፀን አይኖራቸውም።
እነዚህ ሰዎች የወር አበባ አያዩም። አያረግዙም። ከወንዶች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አስቸጋሪ ሊሆንባቸው ይችላል።
እንደዚህ ዓይነት የዘረመል ሚውቴሽን እንዳለ ማወቅ አስደንጋጭ ሊሆን ይችላል።
ባለፉት 30 ዓመታት የፆታ ዕድገትን (ዲኤስዲ) ልዩነቶችን ለመፍታት በአህሩስ ዩኒቨርሲቲ የኢንዶክሪኖሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ክላውስ ሆጅብጀርግ ግራቭሆልት “በቅርቡ የXY ክሮሞዞም እንዳለባት ያወቅናት ሴት 33 ዓመቷ ነው” ብለዋል።
ለምን ማርገዝ እንደማትችል ስለማታውቅ ነበር ለመርመራ ስትሄድ ያገኟት።
“ማህፀን እንደሌላት ስለደርሰንበት ልጅ መውለድ አትችልም። በጣም አዘነች” በማለት ተናግረዋል።
ዶ/ር ግራቭሆልት የአንድን ሰው የፆታ ማንነት ከመጠየቅ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንድምታ አለመረጋጋትን ሊፈጥር ይችላል ብለዋል። ብዙ ጊዜ ታካሚዎቻቸውንም ወደ ሥነ-ልቦና ባለሙያ ይልኳቸዋል።
“ፎቶዋን ባሳያችሁ ሴት ነች ትላላችሁ። ሴት አካል አላት፣ ወንድ አግብታለች። እንደ ሴት ይሰማታል። አብዛኞቹ ታካሚዎቼ ሁኔታውም ተመሳሳይ ነው።”
ዶ/ር ግራቭሆልት የወር አበባ አለማየቷን በተመለከተ ለምን ሐኪም እንዳላማከረች ሲጠይቋት በቤተሰቧ ውስጥ ሌላ ትልቅ ሴትም የወር አበባ ስለማያዩ የተለመደ ነገር መስሏታል።
ዶ/ር ግራቭሆልት ያጋጠማቸው ሌላ የዘረመል ሚውቴሽንም አለ።
በብዛት በሴቶች ውስጥ የሚገኙትን XX ክሮሞዞም ያላቸው ወንዶችንም መርምረዋል። “እነዚህ ወንዶች መካን ናቸው። እንደ ማንኛውም ወንድ ናቸው። የዘርፍ ፍሬ ማምረቻቸው አነስተኛ ሲሆኑ የወንድ የዘር ፍሬ አያመርቱም። ይህንን ሲያውቁ ሁልጊዜም በጣም ይጎዳሉ። ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ከብዙ ወንዶች በተቃራኒ ቴስቶስትሮን ማምረት ያቆማሉ።”
በአንዳንድ ባህሎች ስለወር አበባ እና ስለሴት የሰውነት አካል በግልጽ ማውራትን አይፈቅዱም። በአንዳንድ አካባቢዎች ሴቶች በሰውነታቸው ውስጥ ያልተለመደ ነገር እንዳለ ለመረዳት የሚያስችላቸውን ትምህርት ላያገኙ ይችላሉ።
ለዚያም ነው ብዙዎቹ ዲኤስዲዎች በጭራሽ አልተመረመሩም ብለው ባለሙያዎች የሚያምኑት። ይህም አጠቃላይ መረጃው በጣም አነስተኛ ያደርገዋል ማለት ነው።

የፆታ ውዝግቡ ኦሊምፒክ ውድድሮችን ይለውጣልን?
ልዩ የፆታዊ ዕድገት (ዲኤስዲ) ያላቸው ሰዎች በስፖርት ውስጥ የተሻለ ጥቅም አላቸውን? አጭሩ መልስ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ የለም የሚል ነው።
ፕሮፌሰር አለን ዊሊያምስ “አንዳንድ ዲኤስዲ ያላቸው ሰዎች በሴቶች ላይ የተወሰነ ብልጫ ቢኖራቸው አያስደንቀኝም” ብለዋል። እነዚህም ትላልቅ ጡንቻዎች እንዲሁም ትላልቅ እና ረጅም አጥንቶች ይኖራቸዋል።
በተጨማሪም ከፍተኛ መጠን ያለው የደም ሂሞግሎቢን ሊኖራቸው እንደሚችል ተናግረዋል። ይህም የተሻሻለ የኦክስጂን አቅርቦትን ለሥራ ዝግጁ ለሆኑ ጡንቻዎች ያቀርባል።
አስተያየታቸው ብዙ የዘርፉ ባለሙያዎችን እንደሚወክል ቢገልጹም ግን ተጨማሪ ማስረጃ ያስፈልጋል።
ወደ ኢማኔ ኸሊፍ እና ሊን ዩ-ቲን ስንመጣ ግን ቁጥጥር ሊደረግበት የሚገባ ዲኤስዲ እንዳላቸው ለማወቅ የሚያስችል በቂ መረጃ የለም።
በውድድር ውስጥ በተለምዶ በወንድ እና በሴት ምድቦች ላይ የሚመረኮዘውን ስፖርት መቆጣጠር ውስብስብ ነው። ምክንያቱም የፆታ ጉዳይ በራሱ ውስብስብ እና ሁለትዮሽ ብቻ አለመሆኑ ነው።

አንዳንዶች በሚቀጥለው ኦሊምፒክ የፆታ ምርመራ የግዴታ እንዲደረግ ጥሪ እያቀረቡ ነው። የተባበሩት መንግሥታት በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ልዩ ልዑክ የሆኑት ሪም አልሳሊምም ይህንን ይደግፋሉ።
ዶ/ር ኤማ ሒልተን “ዲኤንኤ መፈተሽ አንደኛው ጉዳይ ነው። በቀላሉ ከጉንጭ ላይ በሚገኝ ናሙና ምርመራም ማድረግ ይቻላል” ብለዋል።
በዚህም ላይ ቢሆን ግን በሳይንቲስቶች መካከል አለመግባባት አለ።
ዶ/ር አለን ዊልያምስ “ከጉንጭ የሚገኘው ናሙና የአንድን ሰው ፆታ እና በስፖርቱ ውስጥ ስለሚኖረው ጥቅም ጠንካራ መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ አያግዝም” ብለዋል።
አጠቃላይ የፆታ ምርመራ እነዚህን ሦስት ጉዳዮች ማካተት አለበት ሲሉም ተከራክረዋል፡
- ጄነቲክስ (የY ክሮሞዞም እና የኤስአርዋይ ‘ወንድ-ፈጣሪ’ ጂንን መፈለግን ጨምሮ)
- ሆርሞኖች (በቴስቶስትሮን ላይ ብቻ የማይወሰን)
- እንደ ቴስቶስትሮን ላሉ ሆርሞኖች የሰውነት ምላሽ። አንዳንድ ሰዎች Y ክሮሞዞም ሊኖራቸው ይችላል። ሆኖም ለቴስቶስትሮን ሙሉ በሙሉ ምላሽ የማይሰጡ ይሆናሉ።
ውድ በመሆኑ ምክንያት ይህ በአሁኑ ጊዜ እየተሠራ አይደለም ብለው ያምናሉ። በጣም ልዩ ዕውቀት ያላቸውን ሰዎችንም ይፈልጋል። ከምርመራ ሂደቱ ጋር በተያያዘም የሥነ ምግባር ስጋቶችም አሉ።
“ይህ ምርመራ አዋራጅ ሊሆን ይችላል። እንደ ጡት እና የመራቢያ አካል መጠን፣ የድምጽ ውፍረት፣ የሰውነት ፀጉር መጠን እና የሰውነት ክፍሎችን መለካትን ያካትታሉ።”
አንድ እርግጥ ሆነው ነገር ይህ ውዝግብ አብሮን ይቆያል። ለአሁኑ ሳይንስ የተለያየ የክሮሞዞም ያላቸው ሰዎች እንዴት መመደብ እንዳለባቸው ግልጽ የሆነ ዕይታን መስጠት አልቻለም። ሕይወታቸውን ከሳይንስ ጋር ላቆራኙ ሰዎች ተስፋ የሚሆናቸው ይህ ጉዳይ በጣም አስፈላጊ የተባለውን ምርምር ስለሚያበረታታ ነው።