የ51 ዓመቱ ዩሱፍ ልክ እንደ ተፎካካሪዎቹ በቴክኖሎጂ የበለጠገ መነፅር ማድረግ አልሻተም።
የምስሉ መግለጫ,የ51 ዓመቱ ዩሱፍ ልክ እንደ ተፎካካሪዎቹ በቴክኖሎጂ የበለጠገ መነፅር ማድረግ አልሻተም።

12 ነሐሴ 2024, 14:29 EAT

ተሻሽሏል 12 ነሐሴ 2024, 14:29 EAT

በሺዎች የሚቆጠሩ አትሌቶች ፓሪስ ከርመው መጥተዋል። ሚሊዮኖች ደግሞ በቴሌቪዥን መስኮት ተመልክተዋቸዋል።

አትሌቶችም ሆኑ ታዳሚዎች ዘንድሮ ወጣ ያለ ነገር የፈፀመ ሰው የበይነ መረብ መነጋገሪያ መሆኑ አይቀሬ ነው።

ላ ደ ፌንስ አሬና ተገኝቶ ብዙዎችን ካስደመመው ዋናተኛ ጀምሮ እጁን በኪሱ አድርጎ የተፎካከረው ቱርካዊ የዒላማ ተወዳዳሪ በይነ መረቡን ነቅንቀውት ነበር።

እነሆ የተወሰኑትን ይዘን ቀርበናል።

ባለግልገል ሱሬው ዋናተኛ

ላ ደ ፌንስ አሬና የተገኙ ታዳሚዎች ዓለማችን አሉኝ የምትላቸው ሰውነተ ፈርጣማ ዋናተኞች ተመልክተዋል።

ለዓመታት ሥልጠና አድርገው በኦሊምፒክ መድረክ ተገኝተው ለመወዳደር ሲዘጋጁ የነበሩትን ዋናተኞች ለመመልከት 17 ሺህ ሰዎች ተገኝተዋል።

ነገር ግን የአንደ ዋናተኛ ቆብ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ወድቆ መድረሻው ሲጠፋ ለእርዳታ እጃቸውን የዘረጉት ተፎካካሪዎች አልነበሩም።

ቀለማም ግልገል ሱሪ ያጠለቀ አንድ ጎልማሳ ታዳሚ ነው ወደ ገንዳው ገብቶ ቆቡን ይዞ የወጣው።

ሕዝቡም በጭብጨባ ተቀብሎታል።

ቄንጠኛው ቱርካዊ ተኳሽ

ቱርካዊው የዒላማ ተኩስ ተወዳዳሪ ዩሱፍ ዲኬች በድብልቅ ፆታ በተካሄደው የ10 ሜትር ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል። በፓሪስ እውቅናቸው ከናኙ ሰዎች መካከል ቁጥር አንዱ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

የ51 ዓመቱ ዩሱፍ ልክ እንደ ተፎካካሪዎቹ በቴክኖሎጂ የበለጠገ መነፅር ማድረግ አልሻተም። ይህም ብቻ ሳይሆን ግራ እጁን በኪሱ አድርጎ ነው የተኮሰው።

ይህ ፎቶው በማኅበራዊ ሚድያ መነጋገሪያ ለመሆን ጊዜ አልፈጀበትም።

ስዊዲናዊው የምርኩዝ ዝላይ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት አርማንድ ዱፕላንቲስ እና የቱርኩ አማካይ ኢርፋን ካን ካቬቺ ድላቸውን ሲያከብሩ ልክ ዩሱፍ ቆመው ፎቶ ተነስተዋል።

ባይልስ እና ቻይልስ ለአንድሬድ እጅ ሲነሱ

አሜሪካዊያኑ ሜዳሊያቸውን ካጠለቁ በኋላ ለብራዚላዊቷ ተቀናቃኛቸው እጅ በመንሳት ደማቅ ክብር ሰጥተዋታል።
የምስሉ መግለጫ,አሜሪካዊያኑ ሜዳሊያቸውን ካጠለቁ በኋላ ለብራዚላዊቷ ተቀናቃኛቸው እጅ በመንሳት ደማቅ ክብር ሰጥተዋታል።

በሴቶች የጂምናስቲክ ውድድር በኦሊምፒክ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ጥቁር ሴቶች ሁሉንም ሜዳሊያ በመሰብሰብ ታሪክ ሠርተዋል።

ብራዚላዊቷ ሬቤካ አንድሬድ ወርቅ ስታገኝ አሜሪካዊያኑ ሲሞን ባይልስ እና ጆርዳን ቻይልስ ደግሞ ብር እና ነሐስ አግኝተዋል።

አሜሪካዊያኑ ሜዳሊያቸውን ካጠለቁ በኋላ ለብራዚላዊቷ ተቀናቃኛቸው እጅ በመንሳት ደማቅ ክብር ሰጥተዋታል።

በዓለማችን በርካታ ሜዳሊያ በመስብሰብ ቁጥር አንድ የሆነችው ጂምናስቷ ባይልስ በፈገግታ ታጅባ ነው ለአንድሬድ ክብር የለገሰችው።

ጆርዳን ቻይልስ የነሐስ ሜዳሊያውን ብትወስድም አራተኛ የወጣችው ሮማኒያዊት አና ባርቦሱ ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት ሜዳሊያዋን ተነጥቃለች።

‘የፖሜል ሆርስ’ ተወዳዳሪው

ስቴፈን ተራደው ከመድረስ በፊት ለበርካታ ደቂቃዎች ያለምንም እንቅስቃሴ መወዳደሪያውን እየተመለከተ ሲጠብቅ ነበር።
የምስሉ መግለጫ,ስቴፈን ተራደው ከመድረስ በፊት ለበርካታ ደቂቃዎች ያለምንም እንቅስቃሴ መወዳደሪያውን እየተመለከተ ሲጠብቅ ነበር።

ፖሜል ሆርስ በተሰኛው ውድድር የተወዳደረው አሜሪካዊው ስቴፈን ኒዶሮሰቺክ መነጋገሪያ የሆነው በምስጠቱ ነው።

ስቴፈን ተራደው ከመድረስ በፊት ለበርካታ ደቂቃዎች ያለምንም እንቅስቃሴ መወዳደሪያውን እየተመለከተ ሲጠብቅ ነበር።

ተራው ደርሶ ወደ መድረኩ የወጣው ስቴፈን መነፅሩን ጥሎ አስደናቂ ብቃት በማሳየት በቡድን እና በግል ባደረገው ውድድር ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ማግኘት ችሏል።

ፈረንሳዊው የምርኩዝ ዘላይ

ፈረንሳዊው አትሌት አዘላሉ ለፍፃሜ ያደርሰው ነበር ቢባልም ወደ ፍራሹ እየተምዘገዘገ ሲመለስ ነው በብልቱ አግዳሚውን የነካው።
የምስሉ መግለጫ,ፈረንሳዊው አትሌት አዘላሉ ለፍፃሜ ያደርሰው ነበር ቢባልም ወደ ፍራሹ እየተምዘገዘገ ሲመለስ ነው በብልቱ አግዳሚውን የነካው።

ፈረንሳዊው የምርኩዝ ዝላይ አትሌት አንተኒ አሚራቲ ለኦሊምፒክ ፍፃሜ ለመድረስ የነበረው ተስፋ በአስገራሚ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ መክኗል።

ምንም እንኳ የተለያዩ ዙሮችን አልፎ ለዚህ ቢበቃም ብዙም መነጋገሪያ ያልነበረው አንተኒ ለፍፃሜው የሚያበቃውን ዝላይ ሲያደርግ ብልቱ እንጨቱን በመንካቱ ምክንያት ከውድድሩ ውጭ ሆኗል።

ፈረንሳዊው አትሌት አዘላሉ ለፍፃሜ ያደርሰው ነበር ቢባልም ወደ ፍራሹ እየተምዘገዘገ ሲመለስ ነው በብልቱ አግዳሚውን የነካው።

የ21 ዓመቱ አንተኒ ጉዳዩን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚድያ ገፁ “አንዳንዴ በብቃት ሳይሆን በብልትም እውቅና ይመጣል” ሲል ፈገግ የሚያሰኝ መልዕክት ፅፏል።

አውስትራሊያዊቷ ዳንሰኛ

ብሬክዳንስ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ስፖርት ሆኖ ብቅ ባለበት መድረክ መነጋገሪያ የነበረችው አውስትራሊያዊቷ ሬቸል ጋን ናት።

የ36 ዓመቱ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ከደረጃ የወረደ ዳንስ በማሳየቷ የማኅበራዊ ሚድያ ርዕስ ሆናለች።

ሬቸል በሶስት ዙር ውድድር 54 ለ 0 ተሸንፋ ከፉክክሩ ውጭ ሆናለች።

የማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እንደ ካንጋሮ እየዘለለች መድረኩ ላይ እየተጠቀለለች አንዳንዴም በጭንቅላቷ ለመቆም እየሞከረችው ያሳየችውን ዳንስ ተሳልቀውበታል።

የኦሊምፒኩ ድንቅ ፎቶ?

የኦሊምፒኩ ድንቅ ፎቶ

አባባሉም ቢሆን አንድ ፎቶ 1 ሺህ ቃል ይወጣዋል አይደል።

ፈረንሳዊው ፎቶግራፈር ጄሮም ብሮይሌ ያነሳው ፎቶ ብዙ አድናቆት አትርፎለታል። ፎቶ ብራዚላዊው የሰርፊንግ ስፖርት የብር ሜዳሊያ ባለቤት ከውቅያኖሱ በላይ ተንሳፎ ሳለ የተነሳ ነው።

ቻይናዊቷ አትሌትና ሜዳሊያ መንከስ

በአድናቆት ከተመለከተቻቸው በኋላ ሜዳሊያውን ወደ ከንፈሯ አስጠግታ እነሱን ‘ኮፒ’ ለማድረግ ሞክራለች።
የምስሉ መግለጫ,በአድናቆት ከተመለከተቻቸው በኋላ ሜዳሊያውን ወደ ከንፈሯ አስጠግታ እነሱን ‘ኮፒ’ ለማድረግ ሞክራለች።

አትሌቶች ለምንድነው ሜዳሊያውን በጥርሳቸው ነከስ አድርገው ፎቶ የሚነሱት? ይህ ጥያቁ የቻይናዊቷ አትሌት ዡ ያኪንም ሳይሆን አይቀርም።

የነሐስ ሜዳሊያ ያገኘችው ያኪን ከጣሊያናዊያኑ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ ባለቤቶች ጋር ለፎቶ ቆማ ሳለ ሁለቱ አትሌቶች ሜዳሊያቸውን ነከስ ሲያደርጉ ትመለከታለች።

በአድናቆት ከተመለከተቻቸው በኋላ ሜዳሊያውን ወደ ከንፈሯ አስጠግታ እነሱን ‘ኮፒ’ ለማድረግ ሞክራለች።

በቀደመው ዘመን አትሌቶች ሜዳሊያን የሚነክሱት ወርቅ ለመሆኑን ለማረጋገጥ ነበር። ነገር ግን ይህ ባሕል ሆኖ ቀርቷል።

አሜሪካዊው ራፐር ስኑፕ ዶግ

በተለይ ሲሞን ባይልስ በጂምናስቲክ ወርቅ ያስገኘላትን ብቃት ስታሳይ ስኑፕ ዶግ በመገረም ያሳየው ፊት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
የምስሉ መግለጫ,በተለይ ሲሞን ባይልስ በጂምናስቲክ ወርቅ ያስገኘላትን ብቃት ስታሳይ ስኑፕ ዶግ በመገረም ያሳየው ፊት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

አሜሪካዊው ራፐር እና የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር ስኑፕ ዶግ ፓሪስ በተካሄዱ ሁሉም ውድድሮች ላይ ታይቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ናሽናል ብሮድካስቲንግ ካምፓኒ አሊያም ኤንቢሲ ለተሰኘው ጣቢያ ደግሞ አስተያየት ሰጭ በመሆን አገልግሏል።

በተለይ ሲሞን ባይልስ በጂምናስቲክ ወርቅ ያስገኘላትን ብቃት ስታሳይ ስኑፕ ዶግ በመገረም ያሳየው ፊት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

ስኑፕ ዶግ ሎስ አንጀለስ በምታዘጋጀው የ2028 ኦሊምፒክ ባንዲራ ተሸካሚ ይሆን ወይ? አብረን እናየዋለን።