ኢትዮጵያ ከሰሞኑ ከአለም ባንክ ገንዘብ ለማግኘት የተስማማችባቸው ነጥቦች በጨረፍታ ሲዳሰሱ ምን ይመስላሉ?
የአለም ባንክ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያ የ1 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ እና የ500 ሚልዮን ዶላር ብድር ፈቅዶ ነበር።
ታዲያ ከእነዚህ ድጋፍ እና ብድር ጀርባ ባንኩ ምን ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ? መሠረት ሚድያ በአጭሩ እንዲህ ዳስሶታል:
– ኢትዮ ቴሌኮም [40 ፐርሰንት ገደማ የሚሆነውን] ሼር ለሽያጭ ያቀርባል፣ ዘጠኝ የስኳር ፋብሪካዎችም እንዲሸጡ ይደረጋል
– አሁን ካለው የ15 ፐርሰንት የቫት ታክስ በተጨማሪ ከቫት ውጪ ተደርገው የነበሩ (እንደ መድሀኒት) ያሉ ሙሉ በሙሉ በታክስ ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋሉ፣ በዚህም ቫት ለ GDP ያለው አስተዋፅኦ በሶስት አመት ውስጥ በእጥፍ እንዲያድግ ይጠበቃል
– የኤሌክትሪክ ሀይልን አምርቶ መሸጥ ወደ ትርፋማነት ለመቀየር ለሚቀጥለው 4 አመት በተከታታይ በየአመቱ የ40 ፐርሰንት ጭማሪ ተጠቃሚዎች ላይ ይጣላል
– ሀገር ውስጥ ያለውን ፍላጎት ለማሟላት ተብሎ በቆሎ፣ ማሽላ እና ገብስ ወደ ውጪ እንዳይላኩ ተጥሎ የነበረው ገደብ ይነሳል
– ብሔራዊ ባንክን ከተፅእኖዎች ነፃ የሆነ ተቋም እንዲሆን አዳዲስ መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ይደረጋል
– እንደ ኤሌክትሪክ ሀይል፣ ነዳጅ አቅራቢ ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ወዘተ ያሉ ተቋማት ኦዲት የሆነ የፋይናንስ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይጠበቃል
መሠረት ሚድያ!