የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ጂን ካሴያ (ዶ/ር)

ማኅበራዊ የጤና ሥጋት የሆነው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ

ምሕረት ሞገስ

ቀን: August 18, 2024

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከሀብታም እስከ ደሃ አገሮች የጤናውን ዘርፍ ፈትኖና የየአገሮችን ኢኮኖሚ አድቅቆ ዛሬ ላይ ለጤና ሥጋት ከማይሆንበት ደረጃ ተካቷል፡፡

ሆኖም በጦርነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በድርቅና ረሃብ የሚፈተኑ አገሮች ውስጥ ፖሊዮን ጨምሮ የተለያዩ ወረርሽኞች መከሰታቸው አልቀረም፡፡

አንዳንዶቹ በቀደመ ባህሪያቸው ሲከሰቱ አንዳንዶቹ ደግሞ ባህሪ ቀይረው ብቅ እያሉ ነው፡፡ ከእነዚህ አንዱ ረቡዕ ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል የአፍሪካ የኅብረተሰብ ጤና አኅጉራዊ የደኅንነት ሥጋት ነው ብሎ ይፋ ያደረገው የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) ይገኝበታል፡፡ 

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ጂን ካሴያ (ዶ/ር) እንደሚሉት፣ ከዚህ በፊት በቫይረሱ ያልተጠቁ ቡሩንዲን፣ ኬንያን፣ ሩዋንዳንና ዑጋንዳን ጨምሮ በትንሹ 13 የአፍሪካ አገሮች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በሽታው ባልነበረባቸው አገሮች በ2024 ብቻ 2,863 በቫይረሱ የተጠቁ ሕሙማን እንደተመዘገቡና ከእነዚህ ውስጥ 517 መሞታቸውን አስታውቀዋል፡፡

የቫይረሱ ሥርጭት በከፋበት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ፣ በአኅጉሪቱ ያሉ ተጠርጣሪ ሕሙማን ቁጥር በ2022 ከነበረው 7,146 እና በ2023 ከነበረው 14,957 ልቆ በ2024 ወደ 17,000 ከፍ ብሏል፡፡ ይህ የተጠናከረ የቁጥጥር፣ የላቦራቶሪ ምርመራና የንክኪ ክትትል ሥርዓት በሌለበት የተገኘ በመሆኑ ቁጥሩ ከዚህ ሊልቅ እንደሚችልም ይገመታል፡፡

አሁን የተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የጉዞ ገደብ ከሚጣልበት ደረጃ ባያደርስም፣ የየአገሮችን ጥምረትና አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሻ ጠቁመዋል፡፡

እንደ ካስያ (ዶ/ር)፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣ አኅጉሪቱ ከዚህ ቀደም ካስተናገደቻቸው ወረርሽኞች የተለየ አይደለም፡፡ በጤና ሥርዓት ውስጥ የተከሰተ ቀውስ በመሆኑ ግን በትብብር መሥራትን ይጠይቃል፡፡

ከግንቦት 2022 እስከ ሐምሌ 2023 ድረስ ቫይረሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት የሚሻ ድንገተኛ የማኅበረሰብ ጤና እክል ተብሎ በዓለም ጤና ድርጅት ታውጆ ነበር፡፡ ሆኖም አፍሪካ በዚህ ወቅት ያስፈልጋት የነበረውን አስቸኳይ ድጋፍ አላገኘችም፡፡ በመሆኑም በዓለም አቀፍ ደረጃ የነበረው ሥርጭት ሲቀንስ በአፍሪካ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ዓለም አቀፍ አገሮች አሠራራቸውን መቀየር እንዳለባቸና ከአፍሪካ ሲዲሲ ጋር በቅርበት በመሥራት ለአባል አገሮች ድጋፍ እንዲያደርጉም ቀሪ አቅርበዋል፡፡

በአፍሪካ የቫይረሱን ሥርጭት ለማወቅ በተሠራ ውስን ዳሰሳና በተገኘ ማስረጃ መሠረት ሁኔታው በዳሰሳው ግንዛቤ ከተገኘበት በበለጠ ከባድ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በ2022 ድንገተኛ የኅብረተሰብ ጤና እክል ብሎ ካወጀ በኋላ፣ የታማሚዎች ቁጥር ጨምሯል፡፡ የሕመሙ ሁኔታም ከባድ ነው፡፡ የኤችአይቪ ሕሙማንን ከማጥቃቱ ጋር ተያይዞም የሞት መጠን እየጨመረ ነው፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በመጀመሪያ በሰዎች ላይ የታየው በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እ.ኤ.አ. በ1970 ነበር፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ቫይረሱ በተለያዩ አገሮች ታይቷል፡፡ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻ ከ15 ሺሕ በላይ በቫይረሱ ሲጠቁ 537 ደግሞ ሞተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ይህንን ጽሑፍ እስካጠናቀርንበት ዓርብ ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) የተጠረጠረም ሆነ የተረጋገጠ ታማሚ እንደሌለ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) በሽታ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ አማካይነት የሚመጣ ሲሆን፣ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የዕጢ ዕብጠት፣ የጡንቻና የጀርባ ሕመም፣ ሽፍታ፣ የቆዳ ቁስለት እንዲሁም የአቅም ማጣት ከበሽታው ምልክቶች መካከል ይገኙበታል፡፡ ልቅ ግብረ ሥጋ ግንኙነትን ጨምሮ ንክኪ የበሽታው መተላለፊያዎች ናቸው፡፡

ጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተለያዩ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎችን የቅድመ ዝግጅት፣ የቅኝትና የምላሽ እንዲሁም የድንበር ጤና ልየታና አገልግሎት ሥራዎችን የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያና ምላሽ ማዕከል በማቋቋም እየሠራ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

 በተለይም ደግሞ በኬንያ አዋሳኝ ሦስት ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ፣ በሶማሌና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ የመውጫና መግቢያ ኬላዎች እንዲሁም በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከወትሮው በተጠናከረ ሁኔታ የቅኝትና የልየታ ሥራዎች እየተተገበረ ይገኛል ብሏል፡፡

በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን፣ ምልክቶችን የሚያሳይ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያደርግ፣ ወይም በ952 እና 8335 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲያደርግ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Yors Nhaqi

  · 

ቅድመ ጥንቃቐ ምግባር ኣድላይ እዩ።

ካብ ሓሚምካ ሕክምና ተኸላኺልካ ጥዕና።

ሓድሽ ሓበሬታ ካብ ውድብ ጥዕና ዓለም ዝወጸ!

*********

ፖዲዶ ሂበይ (Monkey pox)ካብ ሓደገኛታት ሕማም ምካኑ ውድብ ጥዕና ዓለም ኣዊጁ ኣሎ።

ኣብ ዲሞክራሳዊት ሪፖፕሊክ ኮንጎ ዝጀመረ ፖዲዶ ሂበይ ናብ ሩዋንዳ : ኬንያ : ኡጋንዳ : ደቡብ ሱዳን ቡሩንዲ ማእከላይ ኣፍሪቃ ሊሒሙ ቁልጡፍ ምልባዕ ይገብር ኣሎ ። ዛጊት ኣብ ኮንጎ ልዕሊ 450 ሰባት በዚ ሕማም ሞይቶም ኣለዉ ። ጠቕላላ ሪፖርት ተገይሩ ዘሎ ክሳብ ሕጂ 524 ሞት ከምኡዉን 24’000 ዝተለክፉ ከምዘለዉ ተነጊሩ ኣሎ!

ጠንቂ መተሓላለፊ ፖዲዶ ሂበይ ብምንታይ እዩ?

1.ጾታዊ ርክብ

2.ምትንካፍ ቆርበት ምስ ቆርበት

3.ብምትንፋስ

4.ተቀራሪብካ ብምዕላል ካልእን

ምልክታት ፖዲዶ ሂበይ እንታይ እዮም?

1. ረስኒ: ልዑል ሙቐት፡ መብዛሕትኡ ግዜ ልዕሊ 101.5°F (38.6°C)

2. ሕማም ርእሲ፡ ከቢድ ሕማም ርእሲ

3. ቃንዛ ጭዋዳታት፡ ቃንዛ ኣብ ጭዋዳታት፡ ሕቖን መላግቦታትን

4. ሕበጥ ሊምፍ ኖድስ (ጽክታት) ብፍላይ ኣብ ክሳድን ብርኪን

5. ዕንፍሩር፦ ባህርያዊ ዕንፉርር ኮይኑ፡ መብዛሕትኡ ግዜ ካብ ገጽ ዝጅምር፡ ድሕሪኡ ናብ ካልእ ክፍሊ ኣካላት ዝዝርጋሕ።

6. ድኻም: ኣዝዩ ድኻም ይስምዓካ

7. ቁሪ ቁሪ ምባል: ቁሪ ዝስምዓካ፡ ዋላ ሙቐት ኣካላትካ ንቡር እንተኾነ

8. ቃንዛ ጎሮሮ: ቃንዛ ምውሓጥ

9. ሰዓል: ደረቕ ሰዓል

ከመይ ጌርና ንከላከሎ፤

1. ክታበት: ኣንጻር mpox ምኽታብ።

2. ናይ ውልቂ መከላኸሊ መሳርሒታት: መሸፈኒ ኣፍን ኣፍንጫን፣ ጓንቲ፣ መከላኸሊ ዓይኒ ምግባር።

3. ጽቡቕ ጽሬት፦ ኢድ ብተደጋጋሚን ብጽቡቕን ምሕጻብ።

4. ናይ ቀረባ ርክብ ምውጋድ: ምስ ዝተለኽፉ ውልቀሰባት ወይ እንስሳታት።

#Share ብምባል ህይወትን ብምድሓን ሰብ ንንቅሕ