September 7, 2024 – Konjit Sitotaw 

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የዛሬ ሶስት አመት ገደማ ሀገራቸው በኢትዮጵያ ላይ ጥላ የነበረው የአስቸኳይ ግዜ እቀባ እንዲቀጥል መፈረማቸው ታውቋል።

‘International Emergency Economic Powers’ በተባለው የአሜሪካ የአስፈፃሚ አካል መመርያ ተግባር ላይ የዋለው እቀባ ኢትዮጵያ ላይ የተጣለው ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ነበር፣ በዚህም አሜሪካ ሁኔታው በውጭ ፖሊሲዬ እና ብሄራዊ ደህንነቴ ላይ ስጋት ፈጥሯል ብላ ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህ እቀባ እንዲነሳ የአግባቢ (lobby) ድርጅቶችን በመቅጠር ጭምር እንቅስቃሴ ቢያደርግም እቀባው እንዲቀጥል ተወስኗል።