Mengistu Musie

የኢትዮጵያዊነት ማንነት

ከዘመነ አርበኝነት እስከ ዘመነ ጠባቦች

=========================

መለስ ዜናዊ እና ኩባንያው ኤርትራን አሳልፈው ከሰጡ በኋላ ያውም አሁን እየሰማነው እንዳለው ቢለመኑም አይሆንም የኤርትራ ሕዝብ ነጻነት ይፈልጋል መሪወቹ ደግሞ መልሰው ሊደራደሩን ይፈልጋሉ በሚል ከሰደዱ ብዙ ሳይቆዩ ባድመ በተባለች ቁራጭ መሬት ሰበብ ወደጦርነት ገቡ። ያን ሰሞን ጨርቅ ያሉትን ሰንደቅ አላማ ከእኛ በላይ ላሳር በሚያስብል ከፍ አርገው አውለበለቡት። ጃሎታን ነፍጠኛ ለሚሉት ሰጥተው እንጉርጉሮ (ለቅሶ) ወዘተረፈ ይሉ እንዳልነበር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጭምር ያዜሙት ገቡ። ስሟን መጥራት ይጸየፉ የነበረውን “ይህች፤ ያች” እያሉ የሚጠሯትን ሐገር ላንቃቸው እስኪታይ ዘመሩባት። ይህ የሆነው በአውሮፓ አቆጣጠር 1998-99 መሆኑ ነው። ብዙ ሳይቆዩ መቶ ሽሆች ያለቁበትን ጦርነት አደረጉ። ጦርነቱ ግቡን ሳይመታም አስጨነገፉት። ሰበብ ያረጉት የተባበሩት መንግስታት ወዘተ በሚል ነበር። እውነታው ግን በኋላ የተለዩት እነገብሩ አስራት እሰየ አብርሐ የተናገሩት ነበር። የኤርትራን ሐገራዊ አንድነት ከኢሳያስ በላይ ጠባቂወቹ እነስብሐት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ እና ኩባንያቸው በመሆኑ ነው። አምስት አመት በሁአላ በምርጫ 2005 የሆነውን ታሪክ ዘግቦታል ልለፈው።

የኦሮሞ ብልጽግና ዛሬ

ስህተት የሌለበት እየመረረ የሚዋጥ ሐቅ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የለበሰ ሰው አይደለም። ሰንደቃላማውን በባምፐሩ የቀባ ባለተሽከርካሪ አስቁመው እንዲፈቀፈቅ ሲያረጉ አይተናል። አንድ ሰሞን እነ ወዲ ሻምበል እና ጋዜጠኛ ደጋፊወች በሚል አንድ ድራማ ሰርተው ነበር። ከዚያ ውስጥ ሐገራቸውን የሚወዱ በእርግጥም ለሰንደቃላማቸው ፍቅር ያላቸው እንደ ወዲ ሻምበል አይነት ሰወች ስለነበሩበት ከዚያ ድግስ ከራቫታቸውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አርገው የሄዱት ወደ ድግሱ ያነን ለብሰው ሊገቡ ሲሉ መቀማታቸውን ነግረውናል።

ይህ ኢትዮጵያን ጠል ዘረኛ እና ጽንፈኛ መንግስት የአደዋ በአልን ዜጎች በድምቀት እና በብሔራዊ ስሜት እንዳያከብሩ ሰንደቃላማቸውን እንዳያውለበልቡ በየአመቱ ይከለክላል። ይህን ክልከላ በዜናወች ሁሉ ዘግበውታል። ለመሆኑ ኦህዴድ የተባለውን ጽንፈኛ ቡድን ሰደቅ አላማ ብሎ የሰራው የግብጽ ወይንም የአንድ አረብ ሐገር አይደለም? ከሊቁ እስከ ደቂቁ በጋቢ ጥለት፤ በሴቶች የቀሚስ ጥለት በኩራት የሚላበሱት የጽንፈኛው የኦሮሞ ሰንደቅ አላማ ጸረ ኢትዮጵያ ምልክት አይደለም። ያነን ለዘመናት ብሄራዊ ምልክቴ የሚለውን የባ’ዕድ ባንዲራ እንጅ የኢትዮጵያ ሶስት ቀለማት ሰንደቅ አይደለም።

ታዲያ ሰሞኑን የጽንፈኛው እና አረመኔው ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን የሰማውን ባናውቅም ከውስጥ እስከ ውጭ ካድሬወቹን እና ወዶ ገባ ባንዳወችን የኢትዮጵያ ካባ ሊያለብስ ሲፈራገጥ እያየን ነው። ይህ የሚሆነው ግማሽ ኢትዮጵያን ጦር ሰብቆ እየወጋም ባለበት ሰአት መሆኑ ምን ያህል ሳይታጠቅ ነገር እንደተበላሸበት የሚያሳይ አዲስ የለብ ለብ ኢትዮጵያዊነት መሆኑን እናያለን። የባሰ አታምጣ ይላል ያገር ሰው። መለስ ዜናዊ ስሟን ጠርቷት የማያውቀውን “ኢትዮጵያን” በስም የጠራት በሰሜን በኩል ወዳጁ ጋር ወደጦርነት ሲገባ ነበር። ዛሬ የኦሮሞው ጠባብ ብሔርተኛ ቡድን ኢትዮጵያዊነትን ሰርዞ ኢትዮጵያን በኦሮማዊነት እንፍጠር ብሎ የሚጋጋጥ ደንቆሮ የግእዝ አልፋቤትን ተጸይፎ በባዕድ ፊደል ለመጠቀም የሄደበት እርዝመት እኛ እና ሐበሾች አንድ አይደለንም የኢትዮጵያ አይነታ መለያን ጥንታዊ እና ግዕዛዊውን ስልጣኔ አይነካንም ብሎ የከዳ ሰንደቋን በአደባባይ የፋቀ። የለበሱትን ወጣት ሴት ልጆቻችንን በዱላ እየአስደበደበ ያባረረ ዘረኛ ጦር መጣ ሲባል ኢትዮጵያዊ ለመሆን ሲሯሯጥ አያየን ነው።

አንድ ነገር ግን ልንል ይገባል።ኢትዮጵያዊነት ለባለቤቶቹ በባለቤቶቹ ያምራል። እንደመለስ ሳይሆን እንደዛሬው ጭብጥ ሁኔታ ኢትዮጵያን መውረር ከባድ የሚያረገው ዘረኛው ያዙኝ ልቀቁኝ ስለአለ ሳይሆን የታጠቁ ልጆቿ እንደአያት ቅድም አያቶቻቸው ስለማያስደፍሯት ነው።

እንደምናየው እስኪ ወረድ በሉ እና አርሲ የማይታየው ሰንደቅ ዛሬ በኩራት በፋኖ ይውለበለባል።ጠላት እነዚህን የታጠቁ ጀግኖች ተሻግሮ ሀገር እንደማይቀማ ግን ታሪክም ያለው እውነታም አስረጅ ነው። ስለኢትዮጵያኢነት እና ኢትዮጵያዊ ለመሆን ገና ድርድር ስለሚጠይቅ ሳይሆን መብቱን ለማስከበር ኢትዮጵያዊነቱን ለማስመለስ በዘመተ ጀግና ነው ኢትዮጵያ ኘጻነቷ እና ማንነቷ የሚጠበቅ የሚከበር።፡