September 11, 2024

ጥላቻ ፍቅርን አይወልድም

የጌታቸው ቃለምልልስ እና የሁለቱ የህወሓት አንጃወች ነገር  (ዶ/ር መንግስቱ ሙሴ)

—————————————————-

የጌታቸው እረዳን ቃለምልልስ በርዮት ሚዲያ አዳመጥሁ። ዳግም የህወሓት ሰወች ስለአላማቸው እና ማድረግ ስለሚፈልጉት ዋሽተው አያውቁም። በተለይ በኢትዮጵያ እና ስለአማራ ሕዝብ ሁሌም ያላቸው አቋም የማይለወጥ እና አንድ ብቻ ነው። ያን አቋማቸውን ጎላ አርገው ይናገሩታል ሁሉም የሚናገሩት ለራሳቸው እንወክለዋለን ለሚሉት ሕዝብ ስለሆነ በደንብ እንዲያዳምጣቸው ይፈልጋሉ።

ሁሌም የሚገርመኝ ሁሉም እንዲሰማው በሚፈልጉት በአማርኛ ቃለምልልስም እያረጉ political correctness ያልሆኑትን መስሎ መታየት የሚሉት በብዙ የፖለቲካ ሰወች ሊታይ የሚችልን የአነጋገር ወይም አመላለስ ዘይቤ ፈጽሞ አይጠቀሙም። ጌታቸውም ሆነ ሌሎች የህወሓት አመራር አባላት ሁሉም በአማራ ሕዝብ ላይ ስለሚሰጡት አቋም ላይ ምንም አይነት የተምታታ እንዳይሆን ግልጽነት እንዲኖረው ይፈልጋሉ እና ያኔ በጦርነቱ ከትግራይ ሰራዊታቸው ወጥቶ የአብይ የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ሲከተል እንኳን መጀመሪያ ጌታቸው እረዳ ከአማራ ሕዝብ ጋር የሚያወራርደው ሂሳብ እንዳለ የተናገረውን ጻድቃን ሰሜን ሸዋ ሰራዊታቸው በደረሰበት ወቅትም ደግሞታል። ግልጽነት ይሏል ያነው እናም ከልሂቅ እስከደቂቅ! ከውስጥ እስከ ዲያስፖራ የህወሓት አባላት እና ደጋፊወች ሁሉ ያልተወራረደ ሂሳብ እንዳላቸው በየማህበራዊ ሚዲያወች አሳይተዋል።

የአማራ ሕዝብም በጎንደር፤ በወሎ እና ሸዋ የወረደበት ፍጅት እንደፍጅት አልታየም። የውጭ ሚዲያወች የጋማ ከብቶች እስከ የደረሰ የታጨደ እና የተከመረ እህልን መቃጠል፤ የጋማ ከብቶችን በየመንገዱ መገደልን የተደፈሩ ሴቶችን ብቻ አይደለም አዛውንቶች ሳይቀር የ Washington Post እማል Tears of Wolega ቢዘግብም እነ CNN ያነን አልዘገቡም ወይንም በአማራ ሕዝብ የተወራረደውን ሂሳብ ለማሳየት ፍላጎትም አልነበረም። በተመሳሳይ የህወሓት አጋር የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በወለጋ የአብይ አህመድ ገዳይ ቡድን በመተከል ያፈስ የነበረው ደም ግዙፍ ቢሆንም ለሚዲያ አልበቃም።

በትናንትናው ጳጉሜ 4 ቀን የእርዮት ሚዲያም የነበረው ቃለ ምልልስ ላይ ሌላ ቀርቶ ጌታቸው እረዳ የፕሪቶርያን ስምምነት በእጅ ጽሁፍ ያውም አለማቀፍ አደራዳሪነን ያሉትን አሳይቶ ሲጨምር ምንም አይነት ተቃውሞ አልገጠመውም ያነንም በኩራት ተናግሮታል አኛም አዳምጠናል። አብይ አህመድ ፕሪቶርያ ላይ የወልቃይት፤ የጸለምት እና የእራያን ጉዳይ ተቃውሞ ሲገጥመው ቴሌፎን በመደወል እና የሰየማቸውን ተደራዳሪወችን በማስገደድ ጭምር ተጽእኖ ማድረጉን ጌታቸው ተናግሮታል። እናም ድርድር የተባለው ባዶ ወረቀት ለህወሓት በሚጠቅም ብቻ ተፈርሞ አዲስ አበባ የገባ እንደነበር ነግሮናል። ከዚያ መልስ በኤርትራ እና አማራ ሕዝብ ላይ እና የትግራይን ሕዝብ ዳግም ለመማገድ የወጡ ጉራወች ሁሉ የዚህች ጸረ ሕዝብ ድርጅት አቋም አሁንም በሁለቱም የህወሓት አንጃወች ያውም እኔ የበለጠ ለአማራ ጠላት ነኝ በሚል አነጋገር አሳይቶናል። ኸሁሉም በላይ አሁንም የአንድ ሐገር ልጆችን አሁንም ጠላት ደስ እንዳይለው የሚል አነጋገር መስማት እና እርዮት የተባለ ሚዲያም ይህን አይነት አነጋገር በዝምታ ማለፍ ቢያንስ ኢሞራል እንደሆነ ማሳሰብ በተገባ። እርቅ ሰላም አንድነት ሊነገርበት በሚገባ ሚዲያ ጥላቻን አጠናክሮ የቀጠለው የህወሓቷ አንጃ ያዋጣኛል ያለውን ነግሮናል።

መሳሪያ አለመፍታትን በተመለከተ እና ህወሓት አሁንም ለሌላ ዙር የእርስ በእርስ ፍጅት ልትዘጋጅ የሚያስችል ትጥቅ በኬንያ በተደረገው እና Litraly ፕሪቶርያ የተጻፈውን ፊርማ ያረፈበትን ሰነድ የሰረዘ እንደሆነ እና አብይ አህመድ ዳግም ያቀደውን ህወሓት ኦሕዴድን በመጠቀም በተለይም የትግራይን ሕዝብ ከአማራ፤ የትግራይን ሕዝብ ከኤርትራ ለማጋጨጥ ያቀደው ሲሆን። በጥላቻ ተፈጥራ በጥላቻ ታሪኳን የምትደመድመው ላለፉት 40 አመታት የኢትዮጵያን ፖለቲካ የጥላቻ በማድረግ ወደር የለሽ ስራ የሰራችው ህወሓት ከጌታቸው እረዳ አንደበት የሰማነው ጸጸት እና የይቅርታ ወይንም የእርቅ እና የሰላም አንደበት ሳይሆን አሁንም እንደተዳፈነ ፍም የሚንገበገብ ጥላቻ እና ይቅርታን የማያውቅ ንዴት ነበር።

ይህን ካዳመጥሁ በኋላ “መጥኔውን ለትግራይ ሕዝብ” ብያለሁ!! (ዶ/ር መንግስቱ ሙሴ)