September 13, 2024 – Konjit Sitotaw 

ኦብነግ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ኦብነግ “በግብጽ ድጋፍ የተቋቋመ የኢትዮጵያ ጠላት ነው” በማለት ተናግረውታል በተባለ በበይነ መረብ በተሠራጨ ንግግር ዙሪያ ማብራሪያ ጠይቋል።

ኦብነግ፣ የኤታማዦር ሹሙ ንግግር “መሠረተ ቢስ”፣ “በሕጋዊነቱ ላይ የተቃጣ” እና “በሰላም ሂደቱ ላይ የተፈጸመ ትንኮሳ” ነው ብሏል።

ፓርቲው፣ መንግሥት የንግግሩን “ትክክለኛነት እንዲያረጋግጥ” እና “ትክክለኛ ኾኖ ከተገኘ ከዚህ ጎጂ አስተያየት ራሱን በማራቅ ለሰላም ሂደቱ ያለውን ቁርጠኝነት ባስቸኳይ እንዲገልጽ” ጠይቋል።

መንግሥት ይህን ካላደረገ ግን ኦብነግን እንደ ሕጋዊ ፓርቲ ማየት እንዳቆመ ያሳያል ያለው የፓርቲው መግለጫ፣ ይህም በሰላም ሂደቱ ላይ አደገኛ መዘዝ ይኖረዋል በማለት አስጠንቅቋል።