September 13, 2024 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ላለፉት 4 ዓመታት ሲመሩ የቆዩት ዮሐንስ ( ዶ/ር) በአደሱ ዓመት ከመስከረም 02 ፤2017 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ ባንክን በስራ አስፈፃሚነት ቦታ እንደተሾሙ ተገልጿል።

ዮሐንስ (ደ/ር) በይፋ ስራዉን ከጀመረ 2 ዓመት ተኩል ያስቆጠረዉ አማራ ባንክን በተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ ጫንያሌዉ ደምሴን የሚተኩ አንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

የግዙፉ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት የነበሩት ዮሐንስ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት በፍቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የአማራ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ብሩን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ መሾሙን በዛሬዉ ዕለት አስታዉቋል።

በአመራር የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል ልምድ ያላቸዉ ዮሐንስ አማራ ባንክ በፕሬዝዳንትን የሚመሩ ሁለተኛው ሰዉ ያደርጋቸዋል ።

ከታህሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሥራ አመራር ቦርድ አባል በመሆን ያገለገሉና የኢትዮጵያ ልማት ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና ዋና ኢኮኖሚስት ሆነዉ መስራታቸው ይታወቃል ።

ከመስከረም 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ስራቸውን እስከ ለቀቁበት ድረስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት የነበሩት ዮሐንስ (ዶ/ር) ባንኩን ተዘፍቆ ከነበረበት ችግር አውጥረው የተስተካከለ አቋም እንዲይዝ ማድረጋቸው ይጠቀሳል።

ላለፉት 9 ወራት የአማራ ባንክ በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጫንያሌዉ ደምሴ ሰኞ ዕለት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የካፒታል ምንጮች መግለፃቸው ይታወቃል ።