September 13, 2024 – Konjit Sitotaw 

በእነ ዳንኤል ዮሐንስ ላይ አቃቤ ህግ  ክስ መሰረተ

የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ በቲክቶከሩ ዳንኤል ዮሐንስን ጨምሮ በስድስት ግለሰቦች ላይ ሦሥት ክሶችን መስርቷል፡፡

አቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ ላይ የመሰረተው ክስ አውሮፕላንን አላግባብ በመያዝ፣ በማህበራዊ ሚደያ አማካኝነት በቀጥታ በማስተላለፍ መልካም ስም የሚያጎድፍ ተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒዩተር ስርአት አማካኝነት በማሰራጨት እና የመንግስት ሰራተኛ ኦፊሻላዊ የስራ ግዴታውን እንዳይፈፅም መቃወም እና አለመታዘዝ የሚሉ ናቸው፡፡

በሁለቱ ወንጀሎች ሁሉም ሲከሰሱ የመዝገቡ መጠሪያ የሆነው በቲክቶክ የሚታወቀው ዮሀንስ ዳንኤል በሶስቱም ክሶች መከሰሱ ተመልክቷል፡፡

ለሁለት ሰአታት ሙሉ ከአውሮፕላን አንወርድም፤ ይከስከስ በማለት ሌሎችም እንዳይወርዱ በማሳደም በቲክቶክ ቀጥታ በማሰራጨት ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት በቲክቶክ ስሙ ዮኒ ማኛን ቀጥታ በማስገባት የአየር መንገዱ ስም እንዲጎድፍ አድርጓል የሚለውንም አቃቤ ህግ በክስ መዝገቡ ዘርዝሯል፡፡