ዝንቅ
ሽኖዬ እና ጎቤ

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

ቀን: September 15, 2024

ልጃገረዶች ሽኖዬ ወይም አባቢሌ እያሉ ከቤት ቤትም እየተዘዋወሩ የአዲሱን ዓመት መልካም ምኞታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ወጣቶች ይህን ባህላዊ ጨዋታ የሚጫወቱት በየቤቱና በጎዳና በቡድን በመሆን  ነው።  ከዚህ ባለፈም ወጣቶች ይተጫጩበታል።  በመስከረም ሦስተኛ ሳምንት ላይ ለሚከበረው ኢሬቻ መዳረሻም ይሆናል። በወጣቶች የሚከወነው  የሽኖዬና ጎቤ ጨዋታ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዋና ዋና ከተሞች እየተከበረ ይገኛል። በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶቹ በዓሉን መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከንቲባ አዳነች አበቤ በተገኙበት አክብረዋል። በሥነ በዓሉ ላይ ከንቲባዋ ባሰሙት ንግግር ‹‹ትናንት አበባየሽ ሆይ፣ ዛሬ ደግሞ ሽኖዬ እና ጎቤን በባህላችን ደምቃችሁ በመጨፈር ለአዲሱ ዓመት መልካሙን ሁሉ ለተመኛችሁልን ወጣቶችና ልጃገረዶች ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፤›› ብለዋል። ፎቶዎቹ ይህንን ሁነት ያሳያሉ፡፡

ሽኖዬ እና ጎቤ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ሽኖዬ እና ጎቤ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር