September 15, 2024 

“ካዛንችስ እና አዋሬ ውስጥ ከህንፃዎች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ ናቸው”

(መሠረት ሚድያ)- የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አመራሮች ባሳለፍነው ሳምንት ካዛንችስ ተገኝተው ነዋሪዎችን ባነጋገሩበት ወቅት ካዛንችስ እና አዋሬ ውስጥ ከህንፃዎች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ መሆናቸው እንደተነገራቸው ታውቋል። ይህን የሚያስረዳ የድምፅ ሪከርድ ደርሶናል።

ከበርካታ ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው በቅርብ ቀናት ካዛንችስ ከስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ጀርባ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

መቼ እንደሚፈርስ ግን ትክክለኛው ግዜ አልተነገረንም ያሉት ነዋሪዎቹ ይህም “እንቅልፍ ነስቶናል፣ ከዛሬ ነገ መጥተው ውጡ ሊሉን ይችላል” ብለው ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል።

ይህንና ሌሎች እንደሚፈርሱ የታወቁ ቦታዎችን ጥቆማ ይዘን በምሽቱ የዜና ፕሮራችን ዩትዩብ ላይ እናቀርባለን።