September 15, 2024 

ኢትዮጵያ እና ሶማልያ በተርኪዬ ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ግዜ ተላለፈ

(መሠረት ሚድያ)- በመጪው ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ/ም ኢትዮጵያ እና ሶማልያ ለሶስተኛ ግዜ በአንካራ፣ ተርኪዬ ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ግዜ መራዘሙ ታውቋል።

በሁለት ዙር ውይይት ተደርጎ ውጤት ያላመጣው የሁለቱ ሀገራት ንግግር በሶስተኛው ዙር የተለየ መፍትሄ ሊያሳካ ይችል ይሆናል የሚል ግምት ቢሰጥም በቅርብ ሳምንታት የተከሰቱ አዳዲስ ክስተቶች ይበልጥ ውጥረቶችን አባብሰዋል።

ሀሩን ማሩፍ የተባለ ጋዜጠኛ ውይይቱ እንዲራዘም የተደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በመድረሱ ሀገራቱ ለእሱ ዝግጅት እና ጉዞ ማድረግ  ስለሚያስፈልጋቸው እንደሆነ አስነብቧል።

ሌሎች የቀጠናው ተንታኞች ደግሞ ውይይቱ ላልተወሰነ ግዜ እንዲራዘም የተደረገው ሶማልያ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት እንድትሰርዝ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጧ ነው ብለዋል።