የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ

ከ 5 ሰአት በፊት

ላለፉት ለዓመታት አወዛጋቢ የነበረው እና በእንግዘሊዝ የክለቦች ታሪክ ትልቁ የተባለው ክስ የሚታይበት ጊዜ ቀን ተቆርጦለታል።

በዚህም የአንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስተዳዳሪ በአንድ ወገን ለአራት ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳው ማንቺስተር ሲቲ በሌላ ወገን ሆነው ከሥነ ምግባር ኮሚሽን ዳኞች ፊት ይቆማሉ።

በክሱ ሂደት ማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን የፋይናንስ ህግጋት ጥሷል በሚል የቀረቡበት 115 ክሶች መታየት ይጀምራሉ።

እነዚህ ክሶች በገለልተኛ ችሎት ከሰኞ መስከረም 6/2017 ጀምሮ ይፋ ባልተደረገ ቦታ መደመጥ እንዲጀምሩ ታውቋል። ሆኖም የህግ ጉዳዮች የሚነሱ ከሆነ ግን ሊራዝም ይችላል።

የክፍለ ዘመኑ ታላቅ የስፖርት ክስ በሚል የተጠራው ይህ የፍርድ ቤት ጉዳይ ለ10 ሳምንታት እንደሚቆይ የሚጠበቅ ሲሆን ብያኔው በፈረንጆች 2025 ይሰጣል የሚል ግምት አለ።

ይህ የፍርድ ቤት ጉዳይ በሁለቱም ወገኖች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ውጤት ይዞ ሊመጣ ይችላል።

በአንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግና በአውሮፓ ኃያል የሆነው ሲቲ ለበርካታ ዓመታት የፋይናንስ ህጉን ሲጥስ እና ‘ሲያጭበረብር’ ነበር የሚል ክስ ይቀርብበታል።

ሲቲ የአቡዳቢው ቢሊየነር ቤተሰብ በ5 ሀገራት ካሉት 13 ክለቦች አንዱ ሲሆን ባለሀብቶቹ ያፈሰሱት ገንዘብ የክለቡን ገጽታ ቀይሮታል።

ማንችስትር ሲቲ በ14 የውድድር ዘመኖች ፈፀሞታል ተብሎ ከቀረበበት 115 ክስ መካከል ትክክለኛ የፋይናንስ ማስረጃ አላቀረበም የሚል ተካቶበታል።

ሲቲ የቀረቡበት ክሶችን ስህተት ናቸው በሚል ሁልጊዜም አስረግጦ ይገልጻል። የሲቲ ክስ ላይ ብዙ መላምቶች እየቀረቡ ቢሆንም በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት መግቢያ ላይ ምን ሊበየን ይችላል የሚለውን ማንም መገመት አይችልም።

ማንችስተር ሲቲ በክሶቹ ጥፋተኛ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ ስሙ በዓለም ትልቅ ከሆነው የስፖርት ክስ ታሪክ ጋር በማጭበርበር ቅሌት ተያዘይዞ ይነሳል።

በብያኔው ደግሞ ወደ ታችኛው ሊግ ሊወርድ በሚያስችል ደረጃ ነጥቡ ይቀነሳል አሊያም ከፕሪሚየር ሊጉ ሊባረር ይችላል።

ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ደግሞ በማንቺስተር ሲቲ አንጻባራቂ ድሎች ላይ ጥላውን ማጥላቱ አይቀሬ ነው። ከዚም ባሻገር በአሰልጣኝ እና በተጫዋቾች የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ጥያቄ ይፈጥራል።

አልፎም የዩናይትድ ኪንግደም የባህረ ሰላጤው የንግድና ፖለቲካ አጋር የሆነችው ዩኤኢ ከለንደን ጋር ያላት ግንኙነት ላይ ጥላውን ሊያጠላ የችላል።

በተቃራኒው ሲቲ አሸንፎ ከክሶቹ ነጻ ከሆነስ? – የፕሪሚየር ሊጉ አወዳዳሪ አካል ላይ ትልቅ ጥያቄን ያጭራል።

ሆኖም ውሳኔው ምንም ይሁን ምን ውጤቱ በዚህ ዓመት የውድድር ዘመን ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም።

የማንችስትር ሲቲ 115 ክሶች ምንድን ናቸው?

ማንችስትር ሲቲ በየሚከተሉት ጥፋቶች ተከሷል፡

ክለቡ በአነዚህ ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ህግጋትን ጥሶ ባልተገባ የውድደር ሁኔታ ለራሱ በመፍጠር ባለፉት ዓመታት ያነሳቻው በርካታ ዋንጫዎች ላይ ጥርጣሬን ያስነሳል። የፔፕ ጉዋርዲዮላ ስኬት ላይም ጥላውነ ያጠላል።

ይህንን ችሎት ማን ያሸንፋል የሚለውን መተንበይ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ሲቲ ላይ የሚጣሉት ቅጣቶች በፈጸማቸው ክሶች ክበደት እና ጥልቀት ላይ የሚመረኮዝ ይሆናል። ይህም ሲቲ ወደታችኛው ሊግ በሚልከው ደረጃ ነጥብ ይቀነስበታል ወይስ አይቀነስበትም የሚለውን ይወስናል።

በዚህ ክስ አሸናፊውን የሚለዩ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ሶስት ነገሮች ወሳኝ ናቸው። የመጀመሪያው የትኛው ወገን የተሻለ ጠበቃ አለው የሚለው ሲሆን በመቀጠል ሲቲ የሚያመጣው የትኛውም ሰነድ ምን ያህል ክበደት ይሰጠዋል የሚለው ነው። ሶስተኛው ደግሞ ሾልኮ የወጣ የኢሚል ምልልስ ካለ ነው።

ዋና አሰልጣኙን ጉዋርዲዮላን ጨምሮ የሲቲ አመራሮች ሁልጌዜም ‘እጃችን ንጹህ ነው’ በሚል ስሜት በከፍተኛ በራስ መተማመን ይናገራሉ።

በርካቶች የዚህን ችሎት ብያኔ በጉጉት እየጠበቁ በርካታ መላምቶችን ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ትክክለኛው ውሳኔው የሚገኘው ግን ከገለልተኛው የሥነ ምግባር ኮሚሽን ይሆናል።